Wednesday, 22 August 2012

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓሮቴስታንታዊ መሪ አስተናገደች

ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መቼም የማይነጣጠሉ ነበር ዛሬ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ተሰሚነቷ እየቀነስ አመራሩ አካል ጫና እያሳደረባት እና ቤተ ክርስቲያኗ እንኳን ሲቃጠሉ ሀይ ባይ እያጣች መጥቶ ዛሬ ደግሞ ይህ አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክስ ተፋተው የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ መሪ ለማስተናገድ በቃች፡፡

መቼም ሁላችሁም እንደምትገምቱት ሐይለማርያም ብሎ ፓሮቴስታንት አይኖርም አይደረግም ብላችሁ ተገምቱ ይሆናል ነገር ግን በደቡቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንሰራፍ ያለው የፕሮቴስታንት እምነት ወደድንም ጠላንም አሁን መሪ የተባሉትን ጠቅላይ ሚንስቴር ሀይለ ማርያም ደሳለኝን ሳይቀር  ሰለባ አድርጓቸዋል፡፡ ወላይታና አካባቢውም ቢሆን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተኩረት ባለመስጠቷ ብዙዎቹ ካደጉባት ቤተ ክርስቲያን   አስተምህሮዋን ባለመረዳት ኮብልለዋል፡፡ እግዚአብሔር ወደ እናት ቤታቸው እስኪመልስልን ልንፀልይ ይገባልእኛ የምንሰራቸው የቤተ ክርስቲያናችን ስራዎች ግን በዝተዋል ፡፡


ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ  እንዲሉ የሆነብን ከዚህ የተለየ አይደለም ምንም እንኳ ያለፉት ጠቅላይ ሚኔስቴርምለቤተ ክርስቲያናችን  እንደዋልድባ ገዳም ያሉትን ችግሮች እላያችን ላይደንቅረው መፍትሄ ሳይሰጡት ከማረፋቸው ውጪ ምንም ባያደርጉልንም ከአሁኑ የማይሻልበት ምክነያት አይኖርም   ይህም ምክነያታችን ግን ግልፅ ነው ፡፡ አሁን እየተከሰተ ያለው ችግር የእግዚአብሔር ቁጣ ነው ብሎ የእግዚአብሔርን ሐያልነት ተረድቶ አቅጣጫውን የሚያስተካክል መሪ በሚያስፈልግበት ወቅት እንዲህ ያለ ነገር መስማት ይከብዳል፡፡  የቅርብ ጊዜ ትውስታችንን እንኳን ብናስታውስ ከንቲባ አሊ አብዶ ሰልጣን በያዙበት አመት  ለእስልምና እምነት  መሰጊድ በአዲስ አበባ ያሰሯቸውን ብንቆጥር ከሁሉም አሳዛኝ ያደርገዋል፡፡

የኢትዮጵያን ታሪክ ወደኋላ ዞር ብለን ብንመለከት መሪዎቿ ለቤተክርስቲያን እድገት የሚጥሩ ነበሩ የቱን አንስተን የቱን እንተወዋለን ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሕገ አበውን፣ ሕገ ኦሪትንና ሕገ ወንጌልን አስተባብራ በመያዝየጥበብ ምንጭ፣ የሥርዓት መፍለቂያ፣ የዕውቀት ባሕር ሆና ሁሉ የተሟላላትስን እመቤት ናት። 

በማኅበራዊ አገልግሎቷ ደግሞ የድኩማን መጠጊያ፣ ያዘኑና የተከፉ መጽናኛ፣የማንነትም አሻራ ነች። ለዚህም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በተለያዩገዳማት፣ አድባራት፣ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ የአብነት /ቤቶችተቀዳሚ ተጠቃሾች ናቸው። በተለያዩ ጊዜያት የተንኮልና የክህደት ቋጠሮይዘው የመጡ መስሐቲያን (አሳሳቾችአፍረው የተመለሱት ከአብነት/ቤቶቹ በወጡ የሀገር መሪ መምህራን ነው ብዙ መጥቀስ ይቻለል

 ከዚህም በተጨማሪ ለሀገር መሪ ለሕዝብ አስተማሪ በመሆን ሕዝብን ያገለገሉደጋጎች  በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ናቸው። ሌላው ልንገነዘበውየሚገባ ቁም ነገር ቢኖር ገና ያልደረስንባቸው ብዙ እምቅ መንፈሳዊ ሃብቶችያሉን መሆናቸዉ ነው::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ተቆጥሮናተሰፍሮ የማያልቅ ውለታ የዋሉ፤ እንደ ዓይናችን ብሌን ልንጠብቃቸውየሚያስፈልጉ የተቀደሱ ሥፍራዎቻችን ናቸው፡፡

ለኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ፣ የሥነ-ሥዕል፣ የፊደል፣ የሥነ-ሕንጻ ምንጭነትናአጠቃላይ የሥልጣኔና የትምህርት ማዕከል በመሆን ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉየሀገር ኩራት ናቸው፡፡ በውስጣቸው የሚገኙት ንዋያተ ቅድሳት፣ሥነ-ሕንጻዎችና ቅርሶች ለሀገርና ለወገን ኩራት ከመሆን አልፈው ዓለም አቀፍቅርሶች እስከ መሆንና ለሀገሪቱም በቱሪዝሙ ዘርፍ ከፍተኛ ገቢ እያስገኙ ያሉውድ ሀብቶቻችን ናቸው፡፡

ለመኆኑ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ መሆኑ ለቤተ ክርስቲያን የሚያመጣው ችግር እና ተያያዥ ጉዳዮች ምንድናቸው? ይህ ታዲያ ብዙ ሐተታ የሚፈልግ አየመስላችሁም፡፡በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ የመስለናል እስቲ እናንተም ተወያዩበት እኛ ለወደፊት እንመለስበታለን:: 
ቸር ያሰማን፡፡

No comments:

Post a Comment