Monday, 23 December 2013

‹‹እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጡ ተቃዋሚዎች ከ‹‹ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ጋራ በየዕለቱ እየተገናኘን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሰን ሕንፃውን እንረከበዋለን›› እያሉ ነው

‹‹ከእናንተ ጋራ መሣርያችኹ ቢኖርና በመሣርያችኹ ብትመኩም ከእኛ ጋራ ደግሞ እግዚአብሔር አለ፤ አንፈራም፤ ከዚህ በኋላ ለውጡ ወደኋላ አይመለስም፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/ የአቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ ቂርቆስና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገዳማትና አድባራት ልኡካን በጥናታዊ ውይይቱ ወቅት (ፎቶ: አዲስ አበባ ሀ/ስብከት) 

(ከሃራ ተዋህዶ)
የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመሸጥ የሚታወቁት የ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባዮቹ ዋነኛ አስተባባሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ፣ በቅርቡ በ1.3 ሚልዮን ብር በገዙትና ለቻይና ተቋራጭ ባከራዩት ሲኖ ትራክ መኪና ብቻ በወር ብር 70,000 ገቢ ያገኛሉ፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ለውጥ ለማምጣት የተነሡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተንገላቱበት የግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም. ጥቃት የተሳተፉትና ሞዴል ፴ በማቃጠል የሚታወሱት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ፣ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች ጋራ ስልታዊ ግንኙነት መጀመራቸው የሚነገርላቸውና ለአፃዌ ኆኅትነት እንኳ ሳይበቁ በደ/ምሕረት ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እልቅና ለመሾም ‹‹መቶ ሺሕ ብር እከፍላለኹ›› በሚል ልጆቻቸውን ለረኀብ የዳረጉት መልአከ ብሥራት መልአከ አበባው (ብይዱ ይመር)ስ እነማን ናቸው?


* * *
የካህናቱን፣ የሊቃውንቱን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የምእመናን ተወካዮችን ከ92 – 97 በመቶ ድጋፍ ያረጋገጠው የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናታዊ ውይይት ዛሬ ይጠናቀቃል፤ የጥናቱን ትግበራ የሚቆጣጠርበአፈጻጸምም እየተከታተለ የሚያርምና የሚያስተካክል ራሱን የቻለ አካል እንዲቋቋም ተሳታፊዎቹ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡
‹‹ይህ መዋቅርና አደረጃጀት ስለ መታሰቡ፣ ቅንብር ስለ መደረጉ በቤቱ ስም አመሰግናለሁ፡፡ አባታችን የልማት አርበኛ ናቸው፡፡ በየመንደሩ ያለው አሉባልታ ይህ ነው አይባልም፤ እዚህ ስናየው ግን የተለየ ነው፡፡ የጥናት ዘገባው ቀጥሎ እንድናየው እንጂ ሁከት አያስፈልግም፡፡ ጀርባዬም ፊቴም አንድ ከኾነ በሕግ ለመተዳደር ምን ያስፈራኛል? አስቀድሞ ይህ እንዲህ ይኾናል እያሉ መደንበርስ ምን ያስመለክታል? ወጡም ሊጡም እያሉ ያሉት ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ነው ይህ ኹሉ ጭፋሮ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ለመጠበቅ ከፍተኛ ሓላፊነት ያለበት ቅ/ሲኖዶስ ይውጣ ያለውን ሕግ መደገፍ ተገቢ ነው!!›› /የደብር አስተዳዳሪ/
‹‹አንድ ድጓ ከዲግሪ ጋራ ይወዳደራል ካላችኹ መቼ ነው እውን ኾኖ የምናየው? እውን ይኾናል ወይ? አምስት እንትንየምንላቸው ካልኾኑ በቀር ይህን የሚቃወም አይኖርምና ቶሎ ይተግበር፡፡ ብፁዕ አባታችን ከዚህ የበለጠ ምን ይጠበቃል? ይሄ ነገር ቶሎ የማይተገበር ከኾነና ወደ ኋላ የምታዘገዩት ከኾነ የልብ ልብ እንዲያገኙ ታደርጓቸዋላችኹ፤ እናንተም ተጠያቂዎች ትኾናላችኹ፡፡›› /የመምህራን ተወካይ/
‹‹የማይነካው ተነካ፤ የዘመናት ጸሎቴ ነበር፤ ፍጻሜውም ዛሬ ዛሬ. . .ይለኛል፤ እንግዲህ ጸሎተ ስምዖንን ነው የምጸልየው፤ ጌታዬ የቤተ ክርስቲያንን መዳን አሳይተኸኛልና ባሪያኽን አሰናብተኝ እለዋለኹ፡፡›› /የምእመናን ተወካይ/


ተጨማሪ መረጃውን ይከታተሉ!

No comments:

Post a Comment