- READ THIS ARTICLE IN PDF.
- ከአብረንታንት እና ማይ ለበጣ ሁለት መነኰሳትወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋል፤ በዶንዶሮቃ ከ50በላይ የመነኰሳት እና መነኰሳዪያት ቤት በፖሊስተፈትሿል
- ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
- የአብረንታንቱ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ እንደታሰሩናቸው
- ከ49 ያላነሱ የቤተ ሚናስ መነኰሳት በፖሊስ ይፈለጋሉ
- ‹‹እናንት ምታታሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎች ናችሁ››/የማይ ፀብሪ ፖሊሶች/
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 23/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 30/ 2012)፦ ምሽቱን ወደ ገዳሙ በገቡት ዐሥር ያህል የማይ ፀብሪፖሊሶችና ታጣቂዎች የተወሰዱት ሁለት መነኰሳት አባ ወልደ ጊዮርጊስ ከዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም፣አባ ገብረ ማርያም ጎንዴ ከማይ ለበጣ (የማኅበረ መነኰሳቱ ሰፊው የአትክልት ቦታ) ናቸው፡፡ ሁለቱ አበውመነኰሳት በፖሊሶቹ ተይዘው ከመወሰዳቸው አስቀድሞ በኣቶቻቸው በፖሊሶቹ ፍተሻ እንደተካሄደበትተገልጧል፡፡ ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት መኾኗ የወረዳው አስተዳደር ለገዳሙ ትውፊታዊ ሥርዐትና ክብር መጠበቅ ያለውን የወረደ ግንዛቤ የሚያሳይ ነው፡፡
ትናንት ምሽት በገዳሙ ውስጥ ከተካሄደው ፍተሻ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ዓርብ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2004 ዓ.ም፣ከጠዋት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በዋልድባ ዶንዶሮቃ ገዳም የሚገኙ ከኀምሳ ያላነሱ መነኰሳትናመነኰሳዪያት ቤት ቁልፎች በኀይል እየተሠበሩ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተመልክቷል፡፡
ኻያ ስምንት ያህል የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት የሁለቱን አባቶች መወሰድ በመቃወም ወደ ማይ ፀብሪ ተጉዘውአቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ወረዳ ከተማው ከሚወስደው ፅርጊያ መንገድ ሲደርሱ በፖሊሶቹ የኀይል ርምጃመገታቱ ተነግሯል፡፡ የጉዟቸው መገታት ብቻ ሳይኾን ‹‹መመለሳቸውም አሳሳቢ ነው ብለዋል›› ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የተናገሩ አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ መጠነ ሰፊ ፍተሻ እና እስር ምክንያት በተለይ ከቆላ ወገራ የመጡ ናቸው በተባሉ አርሶአደሮች ድንገተኛ ርምጃ እንዲሁም በጅብ መንጋና በእባብ በፕሮጀክቱ የጥበቃ ኀይል አባላት እና ሠራተኞች የሕይወት እና አካላዊ ደኅንነት ላይ ደርሷል የተባለው ጉዳት ነው፡፡
አስገራሚው ጉዳይ ግን በሽታቸው ይኹን የወቅቱ መገኛቸው አነጋጋሪ ስለኾነው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶመለስ ዜናዊ ጽኑ ሕመም የፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊሶች በመነኰሳቱ ላይ የተናገሩት ቃል ነው - ‹‹እናንተምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡››
በተደጋጋሚ በወረዳው ፖሊስ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተጋልጠው ከሚገኙት የዋልድባ አብረንታንት ቤተሚናስ መነኰሳት መካከል ‹‹ፕሮጀክቱን እንቃወማለን፤ ለገዳማችን ክብር እና ህልውናም እንሰየፋለን›› በሚልግልጽ ተቃውሞ ያሳዩ 49 መነኰሳት ስም ዝርዝራቸው ተይዞ በፖሊስ እየተፈለጉ መኾኑን ምንጮች ከስፍራውገልጸዋል፡፡ ፖሊሶቹ በየጊዜው እየመጡ መነኰሳቱን እየለዩ ለሚያደርሱት እንግልትና እስር ከዋልድባ ቤተ ሚናስ መነኰሳት ጋራ የአስተምህሮ ልዩነት ያላቸው የዋልድባ ቤተ ጣዕማ መነኰሳት ‹‹ተባባሪዎች ናቸው›› ተብሏል፡፡ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም ከዋልድባ አብረንታንት ገዳም በማይ ፀብሪ ፖሊስ ተወስደው የታሰሩትመነኮስ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ አሁንም ያልተለቀቁ መኾናቸውን ምንጮቹ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በተለይም ከሰኔ ወር ጀምሮ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትና የዛሬማ ወንዝ ግድብ በዋልድባ ገዳም ላይከሚያደርሰው ተጨባጭ አደጋ እና ታሳቢ ስጋቶች ጋራ ተያይዞ በፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊስ በማኅበረ መነኰሳቱላይ የሚደርሰው ወከባ፣ እስርና እንግልት ተባብሶ ስለ መቀጠሉ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
የማይ ፀብሪ ፖሊሶች እንደተናገሩት ለገዳማቸው ክብርና ህልውና መጠበቅ የቆሙት ጽኑዐኑ የዋልድባ ማኅበረመነኮሳት ‹ምታታሞች› ባይኾኑም÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ የተያዙበትን ጽኑ ሕመም እንደእግዚአብሔር ተግሣጽ (እንደ መቅሠፍት) የሚቆጥሩ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጥቂት እንዳልኾኑ በሕመማቸው ዙሪያ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚተላለፉ መልእክቶች ያስረዳሉ - ‹‹ደዌ ዘመቅሠፍት›› እንዲሉ፡፡
በርግጥም ሰው ኾኖ መታመም የሚያነጋግር ባይሆንም የታላቁ ገዳም መነኰሳትና ባሕታውያን አባቶች የዘወትርሐዘንና ልቅሶ÷ በተለይም በዚህ የሱባኤያቸው ወቅት÷ ግዳጁን አይፈጽምም ለማለት አይቻልም፡፡
No comments:
Post a Comment