መላእክትን ‹‹ያድናሉ›› ማለት ስሕተት ነውን?
ለመሆኑ መላእክት ማዳን ይችላሉ ማለት ስሕተት ነውን? ዛሬ ዛሬብዙዎች መናፍቃን መላእክትን ‹‹ያድናሉ›› ማለት እንደ ስሕተትና
እንደ ክህደት ቆጥረውት ሲናገሩ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ ለምንሲባሉም መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም››
በማለት ያለአገባቡ ጥቅስ ይጠቅሳሉ፡፡

በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም›› ይላል፡፡ይሁን እንጂ ይህ መላእክት አያድኑም ማለት አይደለም፡፡
ቅዱስ ዳዊት በግልጥ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያይሰፍራል፤ ያድናቸውማል›› ይላል፡፡ (መዝ33.7) ጥቅሱ
‹‹ያድናቸውማል›› ማለቱን ልብ በሉ፡፡ መላእክት የማያድኑ ቢሆኑ ኖሮቅዱስ ዳዊት በዚህ መልኩ ግልጥ አድርጎ ‹‹ያድናቸውማል››
ይል ነበር?መጽሐፍ ቅዱስ ከመሰከረው እውነት የሚበልጥ ዕውቀት አለንን? እርሱ‹‹ያድናሉ›› እያለ እኛ ‹‹አያድኑም›› ብንል ምን
ማለታችን ነው? ይህጥቅስ ውሸት ነውን? ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንታዘዘዋለን?እናምነዋለን? ወይስ ልናርመው እንወዳለን?

በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ንባብ ውስጥ ‹‹ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝመልአክ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ›› በማለት ያዕቆብ የልጅ
ልጆቹንእንደባረከ እናነባለን፡፡ (ዘፍ48.16) በዚህ ጥቅስ ውስጥ መልአክ‹‹ከክፉ ነገር ሁሉ›› እንደሚያድን በግልጽ ተጽፏል፡፡
መላእክት‹‹ያድናሉ›› ላለማለት እነዚህን ግልጽ ቃላት መላእክት ይጠብቃሉ፤ይራዳሉ፤ ያግዛሉ በማለት ማድበስበስ ይኖርብን ይሆን?
ይህ ሁሉዝርዝሩ ሥራቸው ቢሆንም እንደሚድኑም ተጽፏልና ማመንያስፈልጋል፡፡

በዚህ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥየተናገረውን ቃል እናቶችና አባቶችበስእለታቸው ‹‹ቅዱስ ሚካኤል አድነኝ፤ቅዱስ ግብርኤል
ድረስልኝ›› እያሉበመድገማቸው የዋሃን ስለሆኑ መጽሐፍቅዱስ ስለማያውቁ ነው መባል አለባቸው?ቅዱስ ዳዊትና ቅዱስ ያዕቆብ
የመላእክትንአዳኝነት በግልጽ ያወጁት መጽሐፍቅዱስን ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተውስላልተማሩ ይሆን? ወይስ አንድ ሰባኪ
የመላእክትን አዳኝነት ስላስተማረ ‹‹ገድልጠቃሽ›› በሚል መጥላላት አለበት? ዘማርያኑስ በዚህ መልኩመዘመራቸው ሊያስወቅሳቸው
ይገባ ነበር?

መላእክት የእግዚአብሔር ናቸው፡፡ የፈጠራቸው እርሱ ነው፡፡የሚፈጽሙትም የእርሱን ፈቃድ ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ
የእርሱ መሆናቸውን በሚያሳይ አገላለጥ ‹‹መልአኩ፣ የጌታ መልአክ፣መላእክቱ›› እያለ ይጠራቸዋል፡፡ ‹‹የጌታ መልአክ በሕልም ታየው››
እንዲል፡፡ (ማቴ1.20) መላእክት ሲያድኑ ፈጣሪ ሥራ አልሠራም ማለትአይደለም፡፡ መላእክት ያለ እርሱ ፈቃድ ምንም ሊያደርጉ
አይችሉም፡፡ ሥራ እንዲሠሩ የሚፈቅድላቸውና የሚያዛቸው እርሱ ነው፡፡ ስለዚህእነርሱ የሠሩትን ይዘን ‹‹ፈጣሪ ይህን አደረገ ማለት
እንችላለን›› እርሱ አዟቸውና ፈቅዶላቸው እስከ ሠሩት ድረስ እርሱ ሠራ ማለት ነውና፡፡ የሚቀጥሉት ሦስት መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ምሳሌዎች ይህን ሐሳብየሚያስረዱ ናቸው፡፡

ለምሳሌ፡- ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት ጅራፍ እንዲሠሩ አዘዛቸው፡፡ራሱ ግን ጅራፍ አልሠራም፡፡ ቢሆንም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ
እንደሠራ አድርጎ ‹‹የገመድ ጅራፍ አበጅቶ›› ይላል፡፡ (ዮሐ2.15)ዳግመኛም ኢየሱስ ክርስቶስ ማንንም አላጠመቀም ሐዋርያቱ ግን
እንዲያጠምቁ አዟቸዋል፡፡ ያዘዛቸው እርሱ በመሆኑ ‹‹ያጠምቃልእጅግም ደቀመዛሙርት ያደርጋል›› የሚል ወሬ በፈሪሳውያን ዘንድ
ተሰምቷል፡፡ ራሱ ግን ማንንም አላጠመቀም ነበር፡፡ (ዮሐ4.1-3) ሌላምሳሌ ለመጨመር እነ ሐና እና ቀያፋ ራሳቸው ኢየሱስ
ክርስቶስን አልሰቀሉትም፡፡ ነገር ግን ተባባሪዎችና ትእዛዝ ሰጪዎች ስለነበሩ ቅዱስጴጥሮሰ ‹‹እናንተ በሰቀላችሁት›› ሲል ሰቃዮች
መሆናቸውን ጠቅሶወቅሷቸዋል፡፡ (የሐዋ4.10)

በአንጻሩ ደግሞ ሥልጣኑ የፈጣሪ ነው ማለት መላእክት ‹‹ይህን ሠሩ››አይባልም ማለት አይደለም፡፡ ፈጣሪ በመላእክት ሲሠራ
መላእክትን እንደ ቁስ ቆጥሮ ይሠራባቸዋል ማለት አይደለም፡፡ መላእክት ሕያዋንናቸው፡፡ የማዘንና የመደሰት ስሜት አላቸው፡፡ ያ
ባይሆን ኖሮ ንስሐበሚገባ ኃጢአተኛ ደስ እንደሚላቸው አይጻፍም ነበር፡፡ ስለዚህመላእክት ደስ እንደሚሰኙ ሁሉ ያዝናሉ ማለት ነው፡፡
ፈጣሪ ሲያዛቸውበፈቃደኝነት ይታዘዛሉ፡፡ ፈጣሪ በእነርሱ ይሠራል ማለት ያለፈቃዳቸውይልካቸዋል ማለት አይደለም፡፡ እንደ ሰው ልጅ ነጻነት አላቸው፡፡ቢሆንም
በእርሱ ፈቃድ ደስ ስለሚላቸው ከፈቃዱ ፈቀቅ አይሉም፡፡ ነጻፈቃድ ባይኖራቸው ኖሮ ሰይጣን በደለኛ ሆኖ አይገኝም ነበር፡፡
የሰይጣንወደ ገዛ ፈቃዱ ማዘንበል ለመላእክት የተሰጣቸውን ነጻነት ያሳያል፡፡ታዲያ ሥራቸውን ወደው የሚሠሩ ሆነው ሳለ ፈጣሪ
ልኮአቸው መላእክት ቢያድኑ ‹‹አላዳኑም›› እንዴት እንላለን? ለማዳን ፈቃደኛሆነው እስካዳኑ ድረስ ‹‹አድነዋል፣ ያድናሉ›› ማለት
የሚገባአይደለምን?

መላእክት እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው የሠሩትን ሥራ እነርሱአልሠሩትም ካልን ሰይጣን የፈጸመውን የጥፋት ተግባር ማን ሠራውልንል
ነው? መቼም እግዚአብሔር ሳይፈቅድለት ሰይጣንም ቢሆንያሰበውን ማከናወን እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ታዲያ ሰይጣንየሠራውን ፈቃጁ
አካል እግዚአብሔር ስለሆነ ፈጣሪ ይህን አደረገ እንጂሰይጣን ይህን አልሠራውም እንላለንን? እንዲሁም ፈቃጁና አዛዡምንም ፈጣሪ
ቢሆን ቅዱሳን መላእክት የሠሩትን እንደሠሩት ማመንናመመስከር ይገባል፡፡ ለክፉ ሥራው ሰይጣን ኃላፊነቱን እንደሚወስድሁሉ
ቅዱሳን መላእክትም ለሥራቸው ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡ ስለዚህፈጣሪ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ቂርቆስንና ኢየሉጣን ስላዳነ ‹‹ቅዱስ
ገበርኤል አዳናቸው!›› የሚገባ ነው፡፡

በቅዱሳን መላእክት ማዳንና ተራዳኢነት ውስጥ የእግዚአብሔርሥልጣንና አዛዥነት በረቂቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን
በምንም መንገድ ቢሠራ በዛ ውስጥ የእርሱ ሥልጣንና ሥራየማይጠረጠር ነው፡፡ መላእክት ያለ ፈጣሪ ትእዛዝና ፈቃድ አንዳችሊሠሩ
አይችሉም፡፡ ፈጣሪ ግን ያለ መላእክት አጋዥነት የፈለገውንየሚሠራ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ፈጣሪ ይህን ሠራስንል
መላእክትን ላይጨምር ይችላል፡፡ መላእክት ይህን አደረጉ ስንልግን በምንም ተአምር ከፈጣሪ ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ
መናፍቃን ‹‹ጌታ፣ እግዚአብሔር ይህን አደረገ›› ብቻ እንድንልየሚፈልጉት ቅዱሳንን ላለማስገባት ነው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ቅዱሳን
መላእክትንና ቅዱሳን ሰዎችን ይህን አደረጉ የምንለው እግዚአብሔርንከማመን ጋር ስለ ቅዱሳን ክብር ለመመስከር ነው፡፡

እሳት በባሕርይው የሚፋጅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንጨትና ብረት ግንብቻቸውን ሳሉ ቢነኳቸው አያቃጥሉም፡፡ ነገር ግን ከእሳት ጋር
ከተዋሐዱ /ከጋሉ/ በኋላ ቢነኳቸው ይፋጃሉ፡፡ እሳት የተዋሐደውብረት የማያቃጥልበት ምንም ሁኔታ የለም፡፡ ካላቃጠለ ወይ እሳት
አልተዋሐደውም ወይም ደግሞ እሳቱ ራሱ አያቃጥልም ማለት ነው፡፡እንደዚሁም እግዚአብሔር በባሕርይው አዳኝ ነው፡፡ መላእክት
አያድኑም ካልን ወይ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር አይደለም ማለት ነውወይም ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ አያድንም እንደማለት
ይቆጠርብናል፡፡ ስለዚህ ‹‹መላእክት ያድናሉ›› ስንል የሚያድን እግዚአብሔር ከእነርሱእንደማይለይ እየመሰከርን መሆኑን ልብ
ማለት ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን!
ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ
No comments:
Post a Comment