Friday, 20 December 2013

ምጽዋት - እዉነተኛዉ የተፈጥሮ ሚዛን

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

አንድ ገዳም ዉስጥ የሚኖሩ አንድ አባት አዉቃለሁ፡፡ እኝህ አባት ሁል ጊዜ የሚናገሩት በምሳሌና በተዘዋዋሪ ነዉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለእርሳቸዉ እንግዳ የሆነ ሰዉ ነገራቸዉን ቶሎ ላይረዳዉ ይችላል፡፡ በአንድ ወቅት ከጓደኛየ ጋር ሆነን ስለ ምጽዋት ስናነጋግራቸዉ በአሁኑ ጊዜ ከጠቃሚነቱ ይልቅ ጎጂነቱ ያመዝናል የሚለዉ ሰዉ እንደሚበዛና በርግጥም ይህን ሊያስብሉ የሚችሉ ብዙ አጭበርባሪዎች መኖራቸዉን ነገርናቸዉ፡፡ እርሳቸዉም ዝም ብለዉ ካደመጡን በኋላ የሚከተለዉን ታሪክ ነገሩን፡፡ በንጉሡ ጊዜ ፈረንጆች መጥተዉ አንድ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቄዉም ጥቁር ነገር ለዓለማችን ጠቃሚ ስላልሆነ ከምድር ልናጠፋዉ እንፈልጋለን፤ የእርሰዎ ሃሳብ ምንድን ነዉ? የሚል ነበር፡፡ እርሳቸዉም ጎጂማ ከሆነ መጥፋት ይኖርበታል፤ ግን ጎጂነቱን አረጋግጣችኋል? ደግሞስ ምንም ሳታስቀሩ ሁሉንም ልታስወግዱ ቆርጣችሁ ተነስታችኋል ? ሲሉ ጠየቛቸዉ፡፡ እነርሱም አዎን ፤ ጥቁር ነገር ለሥልጣኔና ለመልካም ነገር እንደማይስማማ ደርሰንበታል፤ ካጠፋንማ የምናጠፋዉ ሁሉንም ጥቁር ነገር ነዉ አሏቸዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡም፡- ጥሩ የምትጀምሩትስ ከየት ነዉ፤ ከነጮች አገር ነዉ ወይስ ከጥቁሮች? ይላሉ፡፡ ፈረንጆቹም ሃሳባችንን እየተቀበሉት ነዉ ብለዉ እየተደሰቱ ፤ የምንጀምረዉማ በእኛ ሀገር ካለዉ ጥቁር ነገር ነዉ ሲሉ መለሱላቸዉ፡፡ እንደዚህ ከሆነና ምንም ምን የጥቁርን ትንሿንም ሳትንቁ በሀገራችሁ ካለዉ ማጥፋት የምትጀምሩ ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ዐይናችሁ ዉስጥ ያለችዉንም ጥቁር ነገር ንቃችሁ መተዉ የለባችሁም፡፡ እንዲያዉም ዋናዉ የሰዉነታችሁ ክፍል ላይ በመሆኗ ከእርሷ መጀመር አለባችሁ አሏቸዉ፡፡ የሚያነጋግሯቸዉ ፈረንጆችም በዚህ ጊዜ ደንገጥ ብለዉ ለካ ጥቁር አስፈላጊ ነገር ነዉ አሉ፡፡ ይህን ከነገሩን በኋላ አባ እንደ ልማዳቸዉ ያለምንም ተጨማሪ ማብራሪያ ዝም አሉ፡፡

Tuesday, 17 December 2013

''''''''''''''''''''''በጎቹና ፍየሎቹ """"""""""""

የሚከተለውን ምንባብ በጥንቃቄ አንብቡ
"""""""""""""""""""""""""""""""''''

(በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ....ምንጭ፡ሐመር የካቲት 2003 ዓ.ም. )
ከዕለታት በአንዱ ቀን በአንድ ሀገር ትልቅ የበጎች በረት ነበረ፡፡ በዚህ የበጎች በረት ውስጥ ብዙ በጎች ይኖሩ ነበር፡፡ ይህ የበጎች በረት ለረዥም ዓመት የቆየ እና ብዙ ታሪክ ያለው በረት ሲሆን በጎቹ ሁሉ ግን የሚኖሩበትን በረት ጥንታዊነት እና ታሪክ በሚገባ የሚያውቁ አይደሉም፡፡ በቅርብ ጊዜ ከሚወለዱት በጎች መካከል ለመስማት ፈቃደኞች ያልሆኑ አሉ እንጂ በረቱን እስከ ዛሬ ድረስ ጠብቆ ለማቆየት ብዙ በጎች ከሚያገሳ አንበሳ ጋር ጭምር ተታግለው ብዙ ድል አድርገዋል፡፡ ብዙ በጎችም ለዚሁ በረት መቆየት ሲሉ አንገታቸውን እስከመስጠት ድረስ ደርሰው ነበር፡፡ ከአሁኑ በጎች ውስጥ ግን አንዳንዶቹ እንኳን ራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው ሊሰጡ የቀድሞዎቹ በጎች የፈጸሙትን ገድል እንኳን ለማመን ይከብዳቸዋል ፤ ለመስማትም ይሰለቻሉ፡፡

Monday, 16 December 2013

እውን ‹‹ተሐድሶ›› የለምን?

በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ

ሰሞኑን በተደጋጋሚ ‹‹ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው ወሬ ነው!›› የሚል ንግግር በመስማቴ ይህንን አጭር ማሳሰቢያ ለመጻፍ ተነሳሣው፡፡ በእርግጥ ንግግሩን ቀደም ሲልም ሰምቼው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን መደጋገሙ ሲበዛ በተለይም ግምት የሰጠዋቸው ሰዎች ነገሩን ተቀብለዉት ስመለከት ለካ የሚናቅ ሐሰት የለም አሰኘኝ!

‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው ወሬ ነው!›› ለሚለው ለምን ፈጠረው? ይህን ሐሳብ ፈጥሮ ምን ይጠቀማል? ቢፈጥረውስ እናንተ ተሐድሶ ካልሆናችሁ ምናችሁ ይነካል? የሚል የራሴን ጥያቄ ፈጥሮ ከመጠየቅ በቀር እኔን ስለማይመለከተኝ የማኅበሩ የቤት ሥራ ነውና ራሱ ይጨነቅበት ብዬ አልፌዋለሁ፡፡ ትንሽ ማብራሪያ ለመስጠት የምሞክረው ‹‹ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም›› በሚለው አመለካከት ላይ ነው፡፡

የሴት ራስ ወንድ

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለጊዜዉ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የሃይማኖት ዐምድ ‹‹ሃይማኖት እና ሴቶች›› በሚለዉ የመወያያ ርእሰ ጉዳይ ላይ ከእኛ እምነት አንጻር ያቀረብኳትን ትንሽ መጣጥፍ እነሆ ብያለሁ፡፡

ቤልጄየም ዉስጥ በምትገኘዉ የአንትወርፕ ከተማ አይሁድ ይበዙባታል፡፡ በዚሁ ምክንያት በዚያ ሀገር ሱቆች እንኳ ሳይቀር በብዛት የሚይዙት ለአይሁድ የሚሆኑትን ልብሶችና ሌሎች የእነርሱን ፍላጎት የሚያሟሉ ነገሮች ነዉ፡፡ ምክንያቱም በዚያ ለሁለት ሺሕ ዐመታት በተሰደዱባቸዉ ቦታዎችም ባሕላቸዉንንና ዕሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ የሚኖሩ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ የተማሩት ትምህርትና የደረሱበት ሥልጣኔና ዘመናዊነት ምንም ያህል ተጽእኖ እንዳያመጣ አድርገዉ መቛቛማቸዉም ሥልጣኔና ዕሴትን አንዴት አስታርቆ መሔድ እንደሚቻልም ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡


Saturday, 14 December 2013

ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትን የአ/አ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናት በመድረክ ለመሞገት አቅም ያነሳቸውና ውይይቱን ለማደናቀፍ ሲያሤሩ የቆዩ ጥቅመኛ የአጥቢያ አለቆችና የአስተዳደር ሠራተኞች በቦሌ ላሊበላ ሆቴል ኅቡእ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው፤ ሤረኞቹ ‹‹ይደግፉናል›› በሚል የሚነግዱባቸው አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸውን ከሤራው እንዲያገሉና ለቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዲቆሙ ይጠየቃሉ!!


ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር ባካሄደው የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተሳትፎ እንዲዳብርና በቋሚ ሲኖዶሱ አማካይነት በሥራ ላይ እንዲውልበመወሰን በሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናታዊ ውይይት ለማወክ አፍራሽ ተግባራትን ሲያራምዱ የቆዩ ጥቅመኛ የአድባራት አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞችበቦሌ ላሊበላ ሆቴል ኅቡእ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰማ፡፡

Friday, 13 December 2013

....የይሁዳ ሰላምታ የቀሪ ሒሳብ ማስተካከያ ነው!!


ከብርሃን ብሂል
ከፌስቡክ ገጿ ላይ የተወሰደ

ሰሞኑን ከሀዋሳ ንፋስ ማዶ አንድ ወሬ ሰማን እነ……….ይቅርታ ጠየቁ አሉii
ማንም ሰው ስለበደሉ ይቅርታ መጠየቁ አጀብ የሚያሰኝ የሚያስመሰግንም ነው፡፡ ስንፀልይም “…..የበደሉንን ይቅር እንደምንል….. እንል የለ? ግን የሰዎቹ ጥፋት የሰው ነው ወይስ የሃይማኖት?(ሰዎቹ የበደሉት የሀዋሳን ምእመን ነው ወይስ ሃይማኖታችንን)? ታዲያ የሃይማኖት በደል በጉልበት(በሰዎች ፊት) በመንበርከክ ይቅርታ ይባላል እንዴ? የሰው በደልስ ቢሆን ልብ ካልተንበረከከ ጉልበት ቢንበረከክ ምን ዋጋ አለው፡፡ የሃይማኖት በደል ግን በኃያሉ በእግዚአብሔር ፊት እራስን አዋርዶ በንስሃ በመመለስ፣ በቀኖና ቤተክርስቲያን፣ በእግዚአብሔር ቃል…. ሂድና እራስህን ለካህን አሳይ…. እንጂ፡፡


Tuesday, 10 December 2013

ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የወጡ (ያፈነገጡ) ሰዎች የሚመለሱት እንዴት ነው? በ(ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ)

December 11, 2013
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ (ከፌስቡክ ገጹ ላይ የተወሰደ)

፩. የቤተ ክርስቲያን ምንነት፣ ዓላማና ተልእኮዎች

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትባለው በአጭር ቃል የኢየሱስ ክርስቶስ አካል ስትሆን፣ አማንያን ደግሞ የተለያዩ የአካል ክፍሎቿ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ባለቤቷና መሥራቿ እግዚአብሔር ሲሆን ከእግዚአብሔር ጋር መንፈሳዊ ኅብረትና ግንኙነት ያላቸው መንፈሳውያን አንድነት (ጉባኤ) ናት፡፡ አንድ ሰው በሃይማኖትና በምሥጢራት አማካይነት ወደዚህች ጉባኤ ሲገባ የዚህ ጉባኤ (ኅብረት) አካል ሆኖ ይሠራል፡፡ ሐዋርያው “ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” በማለት ያስረዳው ይህን ነው፡፡ 1 ቆሮ. 1፡9 እንዲሁም “ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም” የሚለው ቃል ይህን የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ እሳቤ ያሳያል። ኤፌ. 2፡19-22 ይህች እግዚአብሔር የመሠረታት ጉባኤ (ማኅበር) ቀዳማዊት ናት፤ “ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ - አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን አስብ” ያለው ለዚህ ነው፡፡ መዝ. 73፡2

የቤተ ክርስቲያን የአንድነቷ መሠረት ሃይማኖት ነው፡፡ ይህ ሃይማኖት ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ አንድና ብቸኛ እውነት ነው፡፡ ሐዋርያው “ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት እንዴት መኖር እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው” ያለው ለዚህ ነው፡፡ 1 ጢሞ. 3፡15 ይህ የቤተ ክርስቲያን አምዷ (ምሰሶዋ) የሆነው እውነትና ሃይማኖት ካልተጠበቀ ወይም ችላ ከተባለና እግዚአብሔር ከገለጠው እውነት ጋር እንሸቃቅጠው ከተባለ ቤተ ክርስቲያን ባሕርይዋ ስለማይፈቅድላት እንዲህ ያለ ነገር መቀበል አትችልም፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሠረቷ እና ዓምዷእውነት ነውና፡፡

የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

December 5, 2013 
(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

ኄኖክ ያሬድ



የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡