Friday, 15 March 2013

13 አክራሪዎች ከ27 መሳሪያ ጋር ተያዙ


(አንድ አድርገን መጋቢት 6 2005 ዓ.ም)፡-በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ወይም በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ  የእምነት ቡድኖች እንዲህ ናቸው ብሎ ለመሰየም የሚያስችል ገላጭና ተስማሚ ቃል ወይም ስያሜ መምረጥ ሁልጊዜም ቢሆን አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ ቃሎቹ ገላጭ ናቸው ሲባል አልፎ አልፎ አንድ ላይ ፈራጅ ሆነውም ይገኛሉ፡፡ 

Tuesday, 5 March 2013

ፍቅርና ሃይማኖት - ነፍስና ሥጋ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ


(ምንጭ፡አዲስ ጉዳይ መጽሔት፣ ቅጽ 7፣ ቁጥር 153፣ የካቲት 2005)
 በአሁኑ ጊዜ ‹‹ፍቅር››ን የማይጠራው አለ ለማለት አይቻልም፡፡ አፍቃሪ -ተፈቃሪው፣ አጣይ-አፋቃሪው ፣ ሸምጋይ አስታራቂው፣ የሥነ ልቡና ባለሙያው፣ ጸሐፊ ደራሲው፣ አንባቢ ተርጓሚው፣ ሃይማኖት ሰባኪው፣ ልጅ አዋቂው፣ ከተሜ ገጠሬው ፣...ሁሉም ፍቅር ፍቅር ይላል፡፡ የሁሉም ፍቅር ግን አንድ ነው ለማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ‹‹ አምላክ›› የሚለውን ቃል የምንጠቀመው ሁሉ ‹‹ አምላክ›› በምንለው አካል እንደምንለያየው ማለት ነው፡፡ ለምን ቀናሽ? ለምን ገደልህ? ለምን ከሳህ?ለምን ታመምሽ? ለምን ተጣላህ?... ለሚሉት ድኅረ ፈተና ወመከራ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ መልሳቸው ‹‹ ስለ ምወደው! ስለምወዳት!›› የሚለውነው፡፡ ይኸ የገረማቸውም እረ ለመሆኑ ‹‹ፍቅር›› ራሱ ምንድን ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ በርግጥም ፍቅር ራሱ ምንድን ነው?

Tuesday, 26 February 2013

የ5ቱ እጩ ፓትርያርኮች አጭር የሕይወት ታሪክ


PDF http://bit.ly/YwKqd1:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየም እጩ ፓትርያርኮችን ለመምረጥ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከካህናት፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ከማኅበረ ቅዱሳን፤ እንዲሁም ከምእመናን ጥቆማ እንዲያካሔዱ ተደርጓል፡፡ በተካሔደው ጥቆማ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማውን በግብአትነት በመጠቀም አምስት ሊቃነ ጳጳሳትን በእጩነት በማቅረብ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ከየካቲት 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ውይይት በማካሔድ አምስቱም ሊቃነ ጳጳሳት በእጩነት እንዲቀርቡ አጽድቋል፡፡

Monday, 25 February 2013

ታሪክን የኋሊት “ፓትርያርኩን አትምጡ ስንላቸው መጥተው እኛንም በገማ እንቁላል አስደበደቡን” አቡነ ማቲያስ



  • አቡነ ማቲያስ አቀድሳለሁ ነው የምልዎት  እንዲህ አይነቱ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ምን ይጎዳል” አቡነ ጳውሎስ
  • እንደ ፖሊሶቹ ቁጥር ማነስና ጥንቃቄ ጉድለት የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎች  የፈለጉትን ዓይነት ወንጀል በላያችን ላይ ከመፈጸም የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም” አቡነ ማቲያስ በጊዜው የተነሳውን ተቃውሞ  ሲገልፁ
  • “ፓትርያርኩን አጅበን ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተን ቦልቲሞር ስንደርስ ፤ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረው ተቃዋሚው የፖለቲካ ቡድን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በድንገት ወጥቶ ወረረን ፤ በጣም ቀፋፊ የሆነ ስድብ ውርጅብኝ አወረደብን፡፡
  • አቡነ ጳውሎስ ይጎበኙታል የተባለው ሕንጻ ውስጥ ፈንጂ ተቀብሯል ስለተባለ እርሳቸውና ከእሳቸው ጋር ያሉት 9 ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የፓትርያርክ ምርጫ ላይ ድምጽ እንዳይኖራቸው ለማድረግ ዘመቻ ተጀምሯል

  • የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ከሀገረ ስብከት ተወክሎ ድምጽ እንዳይሰጥ ትዕዛዝ ተላፏል፡፡
  •  ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ያለምንም ተቀናቃኝ የካቲት ሃያ አራት 6ተኛፓትርያርክ ሆነው ይሾማሉ፡

(አንድ አድርገን የካቲት 19 2005 ዓ.ም)፡- የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ባቀረባቸው አምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ዙሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ እጩዎቹን በማጽደቅ ትላንት ጥር 18 2005 ዓ.ም ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ፤ ይህ ይፋዊ መግለጫ 2791 በላይ ጥቆማዎች እንደደረሱት ገልጿል ፡፡ ለእጩነት የተጠቆሙት አባቶች በጠቅላላ 36 ሲሆኑ 15ቱ በአግባቡ ባለመጠቆማቸው እነርሱን ጥሎ አስራ ዘጠኙ ላይ በተቀመጠው የመመዘኛ መስፈርት መሰረት አምስቱን አሳልፎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኮሚቴው ያከናወነውን ስራ አባ አስጢፋኖስ እንዲህ በማለት ገልጸዋል “የአስመራጭ ኮሚቴው ከአምስት ያልበለጡ ከሶስት ያላነሱ እጩ ፓትርያርኮችን የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለማቅረብ ሰፊ ውይይት አድርጓል ፤ በተደረገው ውይይትም አሁን በአገልግሎት ላይ ካሉ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል 19 ሊቃነ ጳጳሳትን በቀጣይነት ለማጣራት አሳልፏል ፤ እጩዎቹን ለመለየት የተከተለው መመዘኛም እድሜና ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡”በማለት ገልጸዋል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ባደረገው ማጣራትም አምስቱን እጩ ፓትርያርኮችን ለይቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቧል ተብሏል ፡፡ እነርሱም 1ኛ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ፤ 2ተኛ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ ፤ 3ተኛ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ፤ 4ተኛ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና 5ተኛ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ  መሆናቸው ታውቋል፡፡ የአምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ስም የቀረበለት ቅዱስ ሲኖዶስም ማጽደቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ “ለመንጋው የሚሆን እረኛ እግዚአብሔር እንዲሰጠን ምዕመናን ፋጣሪያቸው በጸሎት እንዲጠይቁ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል”ብለዋል፡፡ 

ሽማግሌዎች ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አነጋገሩ፤ አስመራጩ መግለጫ ሰጠ


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF) ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት አስምት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።


ከፍተኛ ታቃውሞና የከረረ ተግሳጽ የደረሰባቸውን አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌምን ጨምሮ ሌሎቹ አራት አባቶች የተካተቱበት የአስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማ ለቅ/ሲኖዶስ ቢቀርብም ተጨማሪም ተቀናሽም ሳይደረግበት መጽደቁ ዛሬ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ሐሙስ በሚደረገው ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር የሚያገኘው ተወዳዳሪ ስድስተኛ ፓትርያርክ ተብሎ ይሾማል ማለት ነው።

Sunday, 24 February 2013

የዕጩዎች ምርጫው እንደፈለጉት ያልሆነላቸው ጳጳሳት ሙግት ገጥመዋል


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2013/PDF)፦ የስድስተኛው  ፓትርያርክ  አስመራጭ   ኮሚቴ  በዛሬው   ዕለት  የዕጩዎቹን  ዝርዝር  ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበበት ወቅት ምርጫው በፈቀዱት መልክ አልሔደላቸውም የተባሉ ጳጳሳት ሙግት ገጥመው መዋላቸውን የደጀ ሰላም ምንጮች ገለፁ።


“ፓትርያሪክ እንድሆን የመንግስት ባለሥልጣን አላግባባሁም” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)


‹ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ ይገባቸዋል›› - (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)


(አዲስአድማስ ጋዜጣ፤ የካቲት 17/2005 ዓ.ም

ፌብሩዋሪ 24/2013/ PDF)፦ የምርጫው ሂደት በይፋ ከተጀመረ አንሥቶና ከዚያም በፊት ቀጣዩ ፓትርያሪክ እንደሚኾኑ ብዙ ከተነገረላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በፓትርያሪክነት ምርጫው ከሚሳተፉ ከ800 በላይ መራጮች የምርጫ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሥልጠና ስም በርካታ ገንዘብ ማውጣታቸውን፤ በሕንፃ ኪራይ፣ በሥራ ምደባ፣ በውጭ ተልእኮና በሹመት አሰጣጥ ለብዙዎች ቃል መግባታቸውን፤ ከዚህም አልፎ ቀጣዩ ፓትርያሪክ እርሳቸው እንደሚኾኑ ራሳቸውን ለመንግሥት አካላት ስለ ማስተዋወቀቸው በአንዳንድ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡

Wednesday, 20 February 2013

ሰበር ዜና - አቡነ ሳሙኤል በካህናትና ምእመናንን ጥቆማ (popular vote?) በከፍተኛ ብልጫ መሩ


የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ፣ ካህናትና ምእመናን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባት ሊኾን ይገባል ያሉትን እንዲጠቁሙ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ከተበሰበሰቡት በሺሕዎች ከሚቆጠሩ ካህናትና ምእመናን ጥቆማዎች መካከል፣ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እጅግ ከፍተኛውን የጠቋሚዎች ቁጥር በማግኘት በከፍተኛ ብልጫ መምራታቸውን ለምርጫው ሂደት ቅርበት ያላቸው ምንጮቸ ገለጹ፡፡

ከየካቲት 1 - 8 ቀን 2005 ዓ.ም በተሰበሰበውና ከቅዳሜ የካቲት 9 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው አግባብነት ያላቸው ጥቆማዎች ቆጠራ ከአንደኛው እስከ ሦስተኛ የወጡ አባቶች ማንነት ተለይቷል፡፡ በዚህም መሠረት ካህኑንና ምእመኑን በስፋት ለማሳተፍ በተሰበሰበው ጥቆማ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በእጅግ ከፍተኛ የጠቋሚዎች ቁጥር የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ መምራታቸው ተረጋግጧል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የከፍተኛ ጠቋሚዎችን ቁጥር ማግኘታቸው ተገልጧል፡፡

ኮሚቴው በጠቋሚዎቻቸው ብዛት አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ያገኙትን የተቀሩትን ሁለት አባቶች ማንነት በነገው ዕለት በሚያካሂደው ቆጠራ እንደሚያውቃቸው ይጠበቃል፡፡ የጥቆማውን ውጤቶችና ምልከታዎች እንደ ግብአት (popular vote?) በመያዝ በምርጫ ሕጉ በሰፈረው ድንጋጌ በተጨማሪ መመዘኛዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ የሚያቀርባቸውን አምስት አባቶች የካቲት 14 ቀን እንደሚያቀርብ መገለጹ ይታወሳል፡፡ አሁን ሾልኮ የተሰማው የጥቆማ ደረጃ ውጤት፣ የተጠቀሱትን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከአምስቱ ዕጩዎች ለመካተት ያበቃቸው እንደኾነ ቆይተን የምናየው ይኾናል፡፡

የዜናው ዝርዝር ይቀጥላል፡፡

የውጪውን ጠላት ለመመከት በቅድሚያ የውስጥ ችግሮቻችንን ማስወገድ ይኖርብናል


ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችም” በሚለው መጣጥፍ መነሻነት የተዘጋጀ ….


(ከመልዐከ ብሥራት፣ ቨርጂኒያ/PDF)፦ ጌታቸው ኃይሌ ናቸው ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ።በቅድሚያ ልባዊ ምሥጋናዬና አክብሮቴ ይድረሳቸው፡፡ በዚህ ጽሑፌ የምናገረው በእውነት ለቤተክርስቲያን ለሚጨነቁ ምዕመናንና አገልጋዮች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አንድዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ አሁንም እያለፈች ነው፡፡ እግዚአብሔር አይበለውናምናልባት የከፋው ፈተና ያለው ከፊት ለፊታችን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህም ሰበቡ ችግሮቻችንንበቅጡ ካለመረዳታችንና ከቸልተኝነታችን የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችንችግሮች በተለይ በውጪው ዓለም ምንና ምን ናቸው?