Monday, 18 February 2013

አባ ፓምቦ

ቅድስት ሜላኒያ ስለ አባ ፓምቦ እንዲህ አለችው "ገና መጀመሪያ ጌዜ ከሮም ወደ እስክንድርያ ስመጣ የእርሱን ቅድስና ሰምቼ እንዲሁም አባ ኤስድሮስ ስለ እርሱ ነገረኝና ከዚያም እርሱ ወዳለበት ወደ በረሃው ወሰደኝ። እኔም በሳጥን ውስጥ የታሸገ ሦስት መቶ (300) ወቄት ወርቅ ወሰድኩና የሚፈልገውን ያክል እንዲወስድ ለመንኩት። እርሱ ግን ከተቀመጠበት ሳይንቀሳቀስ ሰሌን እየታታ ባረከኝና "እግዚአብሄር ዋጋሽን ይሰጥሽ ዘንድ ፈቃዱ ይሁን" አለኝ። ከዚያም ረድኡን "ይህን ውሰደውና በሊቢያና በደሴቶች ለሚኖሩት ወንድሞች ለሁሉም አከፋፍላቸው፣ እነዚህ ገዳማት ከሌሎቹ ይልቅ ድሃዎች ናቸውና" አለው። በግብጽ ላሉት ግን  የእነርሱ መሬት የተሻለ ለምነት ስላለው ምንም እንዳይሰጥ አዘዘው።

እኔ ግን ስለ ስጦታዬ የበለጠ እንዲያከብረኝና እንዲያመሰግነኝ ተስፋ በማድረግ እዚያው ቆምኩ። ሆኖም ምንም ሲለኝ ስላልሰማው፣ አባ ውስጡ ምን ያህል እንዳለ ታውቅ ዘንድ 300 ወቄት ነው አልኩት። እርሱ ግን እራሱን እንኳ ቀና ሳያደርግ "ያመጣሽለት እርሱ፣ ልጄ ሆይ፣ መጠኑን የሚነግረው አያስፈልገውም። ተራሮችን የሚመዝን እርሱ የዚህን ወርቅ ክብደት የበለጠ ያውቀዋል። የሰጠሺው ለእኔ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ መንገርሽ አግባብ ነበረ። የሰጠሽው ለእግዚአብሄር ከሆነ ግን የመበለቲቷን ሁለቱን ሳንቲሞች ያልናቀ እርሱ ያውቀዋልና መንገር አያስፈልግሽም" አለኝ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምንም ሳይታመም ቅርጫት እየሰራ እያለ በሰባ ዓመቱ ዐረፈ። ሊያርፍ ሲል እየሰራ የነበረውንና ሊያልቅ ትንሽ የቀረውን ቅርጫት ላከልኝ፣ እንዲህ በማለት፣ "ታስቢኝ ዘንድ በእጆቼ የተሰራውን ቅርጫት ተቀበዪ፣ ታስቢኝ ዘንድ የምተውልሽ ሌላ ምንም ነገር የለኝምና።" ስጋውን ለመቃብር ካዘጋጀው በኋላ ቀበርኩትና ከበረሃው ተመለስኩ። ያቺን ቅርጫትም እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ድረስ በክብር አኖርኋት።

ይህ አባ ፓምቦ ሊሞት ሲል እንዲህ አለ ፦ "ወደዚህ በረሃ ከመጣሁበትና በአቴን ሠርቼ በዚህ መኖር ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በእጄ ያልሰራሁትንና ያልደከምኩበትን ነገር አልተመገብኩም፣ የምጸጸትበት ቃል አልተናገርኩም። ሆኖም ሃይማኖተኛ መሆን ገና ምንም እንዳልጀመረ ሰው ሆኜ ነው ወደ እግዚአብሄር የምሄደው።"

የአባታችን የአባ ፓምቦ ምልጃውና በረከቱ አይለየን። አሜን።

(ከበረሓውያን ሕይወትና አንደበት በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ)
ጥር 2003 ዓ.ም

ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበር ያልቻለባቸውና የማይችልባቸው ምክንያቶች


ይህ ጽሑፍ የአቅማቸውን ጥቂት ነገር ለማድረግ የሚተጉትን ላይመለከት ይችላል።

(ደጀ ሰላም የካቲት 8/2005፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ PDF)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በኢትዮጵያ እየተስፋፋ በመጣው እምነትን በነጻ የማራመድ መብት ገፈፋ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ኦርቶዶክሱ ክፍል ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በወታደራዊው የደርግ ዘመን የነበረውን ግፍና መከራ እንኳን ለጊዜው ብናቆየው “የሕዝብ ብሶት ወለደኝ” ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት ከተመሠረተ ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን በዓይነ ቁራኛ ከመታየት እስከ የ“ነፍጠኛ ጎሬ” እስከመባል ድረስ ብዙ ዘለፋ አስተናግዳለች። ከዚያም ገፋ ሲል በአንዳንድ አክራሪዎች ምእመናኗ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ከየአካባቢው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። ለዚህም በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የሚያራምደው ፖሊሲ ሁነኛ ምክንያት ነው።

Tuesday, 22 January 2013

ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም (ክፍል አንድ)



ይህንን ደብዳቤ ላንቺ የምጽፈው የገናን በዓል ከልቤ የምወደው በዓል ስለሆነ ነው፡፡ የምወደው ደግሞ የገና ዛፍ ተተክሎ፣ በጥጥ ተውጦ፣ በከረሜላ ተከብቦ፣ በመብራትም አሸብርቆ ስለሚያስደስተኝ አይደለም፡፡ እንዲያውም እንዲህ 
ያለው ነገር ብዙም አይመስጠኝም፡፡ ቤተ ልሔም ዋሻ ውስጥ ለተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ዛፍ ማሸብረቅ፣ በረዶ አይታ በማታውቅ ሀገር ውስጥ የበረዶ ምሳሌ የሆነውን ጥጥ ማግተልተል፤ ልጇን የምታለብሰው አጥታ የበለሶን ቅጠል ላለበሰች እናት ከረሜላና ኳስ ማንጠልጠል ለእኔ ትርጉሙ አይገባኝም፡፡ መቼም ፈረንጅ መሆን ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች አንዱ እርሱ ሲያብድ የሠራውንም ቢሆን ፋሽን ነው ብሎ የሚከተለው አለማጣቱ ነውና ምን ይደረግ፡፡

ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም (ክፍል ሁለት)


ድንግል ማርያም ሆይ 


ለፈው እንደሰማሽኝ ዛሬም ትሰሚኛለሽ ብዬ ነገሬን እቀጥላለሁ፡፡ 


አንቺ በቤተልሔም ከተማ ማደርያ አጥተሽ እንደተንከራተትሽው ሁሉ ነፍሰ ጡር ሆኖ ቤት መከራየትማ የማይታሰብ ነው፡፡ አከራዮቹ የልጁን የሽንት ጨርቅ ማጠቢያ፣ የገንፎውን ማብሰያ፣ የጡጦውን መቀቀያ፣ የእንግዳውን ማስተናገጃ ሁሉ አስበው የቤት መሥሪያ ያስከፍሉሻል፤ ያለበለዚያም አንቺን እንዳሉሽ ‹ማደርያ የለም› ይላሉ፡፡ 


እኔማ ሳስበው አሁን አሁን ሕዝቡ መጥኖ መውለድ የጀመረው የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት ገብቶት አይመስለኝም፡፡ አከራዮች ናቸው የሕዝባችንን ቁጥር እየቀነሱት የመጡት፡፡ ልጅ ካለሽ፣ ያውም ከሦስት በላይ ከሆኑ፣ ማን ያከራይሻል፡፡ ብትከራይም ልጆችሽን እንደ ጥጃ ስትጠብቂ መኖርሽ ነው፡፡ ‹ይህንን ነኩ፣ ያንን ሰበሩ፣ ይህንን ቆረጡ፣ ያንን አበላሹ፣ እዚህ ገቡ፣ እዚያ ወጡ› እየተባለ በየቀኑ ሮሮ ነው፡፡ ልጅ ደግሞ በተገዛና በተከራየ ቤት መካከል ያለው ልዩነት አይገባውም፡፡ እና በዚህ ምክንያት ቤት ሳይሠራ ላለመውለድ፣ ከወለደም ከሁለት በላይ ላለመውለድ ስንቱ ወስኗል፡፡ 

Friday, 14 December 2012

ደም መስጠት እና የሰውነት አካልን መለገስ ይፈቀዳል?

በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ
ከፌስቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ

የሰው ልጅ በዚህች የመከራ ቦታ በሆነች ምድር እስካለ ድረስ ብዙ ፈተናዎች ያጋጥሙታል፡፡ ከሰው ልጅ ውድቀት በኋላ ‹‹ራስ ሁሉ ለሕመም ልብም ሁሉ ለድካም ሆኗል ፤ ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም›› ኢሳ. 1.5
ከሚቻለን በቀር እንድንፈተን የማይፈቅደው እግዚአብሔር ‹‹ከፈተናው ጋር አብሮ መውጫውን ያደርግላችኋል፡፡›› ተብሎ እንደተነገረ የሰው ልጅ በተሰጠው ብሩሕ አእምሮ ተጠቅሞ በሚያድንበት የሕክምና ጥበብ እንዲራቀቅ አድርጓል፡፡ እኛ ክርስቲያኖችም ሐኪሙ የአርብ ዕለት ፣ የሚሰጠው መድኃኒት ደግሞ የማክሰኞ ዕለት ፍጥረታት መሆናቸውን በማሰብ የሰው ልጅ ስለደረሰበት የህክምና ጥበብ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ ማዳን የእርሱ ነውና ፤ ሐኪሞቹ ሌላ ፣ ህክምናው ሌላ ቢሆንም ፈዋሹ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እናምናለን፡፡


Monday, 19 November 2012

የቅዱስ ላልይበላ ደብር ካህናትና ምእመናን የመንግሥት ያለህ እያሉ ነው


     ቤተክህነቱ በደብሩ አለቃ የሚፈጸመውን ሙስናና የአስተዳደር በደል መቆጣጠር ተስኖታል
  • የውቅር አብያተ መቅደሱ የቱሪስት ገቢ ተቆጣጣሪ የለውም፤ የቅርሶቹ ጉዳት ተባብሷል
  • በደብሩ ገንዘብ የተሠሩት የቤተ አብርሃም እና ይምርሐነ ሆቴሎች ባለቤት አይታወቅም


አዲስ አድማስ ጋዜጣ የተወሰደ

(አንድ አድርገን ህዳር 10 2004 ዓ.ም)፡-በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የቅዱስ ላሊበላ ደብርየሚያገለግሉ ካህናት እና ምእመናን÷ በደብሩ አስተዳዳር በሚፈጸመው ሙስናና የአስተዳደር በደልመማረራቸውንና አቤቱታቸው ሰሚ አለማግኘቱን ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የቱሪዝም ገቢየግል ሀብትን ለማደለብ እየዋለ መኾኑን የጠቆሙት ካህናቱ÷ በቅርሶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛደረጃ መባባሱን፣ሙሰኝነትንና የአሠራር ብልሹነትን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ ካህናትና ሠራተኞች ለመባረርናለእስር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

Friday, 9 November 2012

እምሊባኖስ ትወፅእ መርዓት




 ኦ ድንግል አኮ በፍተወተ ደነስ ዘተጸነስኪ ፡፡ ድንግል ዘርዕ ዘይወጽእ እምስካበ ተዓዳዌ ሕግ ይከውን ለቅጥቃጤ ወለሙስና ባለው ፈቃድ የተፀነሽ አይደለሽም፡፡ አላ በሩካቤ ዘበህግ እምሐና ወኢያቄኒም ተወለድኪ ክቡር አውስቦ በኵለሄ ወለምስካቦሙኒ አልቦቱ ስዕበት ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ አንድም እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ፡፡ ወበአመፃ ወለደተኒ እ...ምየ እንዲል፡፡ በልተው ጠጥተው በሚያደርጉት ፈቲው ጽነት የተፀነስሽ አይደለም፡፡ ብዝኁ ወተባዝኁ ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ ታሪክ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ በጥሪቃ ይባላሉ፤ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ ፤ ብእላቸውም የወርቅ ፤ የብር የፈረስ ፤ የበቅሎ የሴት የባርያ የወንድ ባርያ ነው፡፡ ከወርቁ ብዛት የተነሳ እንደ አምባር እንደ ቀለበት እያሠሩ ከበሬው ከላሙ ቀንድ ያደርጉት ነበር፡፡ ይህን ያህል አቅርንተ ወርቅ ይህን ያህል አቅርንተ ብሩር ተብሎ ይቆጠር ነበር እንጂ የቀረው አይቆጠርም ነበር፡፡


በጋሻው ደሳለኝና አሰግድ ሣህሉ


(ደጀ ሰላም ጥቅምት 30/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 9/2012, READ THE NEWS IN PDF)፦ሃይማኖት ጉዳይ በተነሣባቸው ጥያቄ ምእመኑ ዓይናችሁን ላፈር ያላቸው ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በተለይ በበጋሻውና በባልንጀሮቹ ላይ ጠበቅ ያለ አጀንዳ እንደተከፈተባቸው ለረዥም ጊዜ ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል። ጉዳዩ በቅዱስነታቸው እረፍት እና በመከካሉ በመጣው ጊዜ ክፍተት ተረሣ ቢመስልም “ይደር” ተባለ እንጂ “ይዘጋ” ስላልተባለ እነሆ ርዕሳችን አድርገነዋል። በድጋሚ። ከበጋሻው እንጀምር።

Thursday, 8 November 2012

ለአዲስ አበባ አራት አህጉረ ስብከት ሥ/አስኪያጆች ተሾሙ



(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የገነገነውን ሙስናና ሌሎችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያቀረበውን ጥናት የመረመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሀገረ ስብከቱ በአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ እንዲደራጅ መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ስለ አከፋፈሉ እና አደረጃጀቱ መነሻ “አቤት ባዩ በዛ፤ ጩኽት በዝቷልና” በማለት የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ ለጋዜጠኞች ያስረዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በየአካባቢያቸው እንዲስተናገዱ በፓትርያርኩ ጊዜ በአባቶችና ሊቃውንት ተጠንቶ ቀጠሮ ተይዞበት የቆየ ጉዳይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡