(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የገነገነውን ሙስናና ሌሎችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያቀረበውን ጥናት የመረመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሀገረ ስብከቱ በአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ እንዲደራጅ መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ስለ አከፋፈሉ እና አደረጃጀቱ መነሻ “አቤት ባዩ በዛ፤ ጩኽት በዝቷልና” በማለት የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ ለጋዜጠኞች ያስረዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በየአካባቢያቸው እንዲስተናገዱ በፓትርያርኩ ጊዜ በአባቶችና ሊቃውንት ተጠንቶ ቀጠሮ ተይዞበት የቆየ ጉዳይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
Thursday, 8 November 2012
ቀሲስ በላይ መኰንን ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲንነት ተነሡ
(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ባለፉት የዜና ዘገባዎቻችን ስንጠቅሳቸው የነበሩትና በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን የነበሩት ቀሲስ በላይ መኰንን ከዚህ ሓላፊነታቸው መነሣታቸው ታውቋል፡፡ የደጀ ሰላም ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰሞኑን በሚደረገው የከፍተኛ ሓላፊዎች ሽግሽግ ቀሲስ በላይ መኰንን የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሓላፊው አማካሪ ኾነው መመደባቸውን እየተነገረ ነው፡፡ በርካታ ዋና ዲኖች በፍጥነት በሚቀያየሩበትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሳይሆን የመቅጫ ቦታ ተደርጎ በሚታሰበው መንፈሳዊ ኮሌጅ ለስድስት ወራት የቆዩት ቀሲስ በላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውሳኔ ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው የታወቀው “በእድሳትና ለዲግሪ መርሐ ግብር መጀመር ይደረጋል በተባለው ዝግጅት” ሰበብ የመንፈሳዊ ኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ከሁለት ወራት በላይ በተስተጓጎለበት፣ ይህንንም ተከትሎ የደቀ መዛሙርቱ (በተለይም የሰሚናር ኮርሰኞቹ) አቤቱታ ጎልቶ በሚሰማበት ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡
Tuesday, 6 November 2012
የኃይለማርያም አጣብቂኝ በመንፈሳዊ ሕይወትና በፖለቲካዊ ማንነት ውስጥ
ከአዲስ ጉዳይ መጽሄትቅጽ 6 ቁጥር 136 ጥቅምት 2005 ዓ.ም
- “እኔ ችግር ያለብኝ ‹እናቴ አልዳነችም› ማለታቸው ላይ ነው ፤ እንደዚህ ማለታቸው ሌሎቹም ሁሉ እንዳልዳኑና እሳቸው ብቻ እንደዳኑ የሚያረጋግጥ ሃሳብ ነው፡፡” ፕሮፌሰር መስፍን
- አቶ ኃ/ማርያም ለቀድሞ ጠ/ሚኒስትር “ዘላለማዊ ክብር እመኛለሁ” ማለታቸውን እንደተጸጸቱበት ተናግረዋል፡፡
- “እናቴ አልዳነችም” ብለው መናገራቸው ራሱ በጣም የሚያሳዝንና ሞኝነት ጭምር ነው፡፡ ይህ እኮ ሁላችንም ማለትም ኦርቶዶክስም ፤ ሙስሊሙና ካቶሊኩ በሙሉ አለመዳናችንን የገለጹበት ቀላል አሽሙር ይመስለኛል” ዶ/ር ያእቆብ
- “አቶ ኃይለማርያም የአቶ መለስን ራዕይ ለማስጠበቅና በሃይማኖተኛነት መካከል እየዋለሉ የሀገሪቱን ሕገ መንግስት ሊጥሱ ይችላሉ” ዶ/ር ያእቆብ
- ዛሬ ስለ ሃይማኖት መጠቃቀስ የጀመሩት የአገር መሪ ነገ ደግሞ ስልጣናቸውን ተጠቅመው እግዚአብሔርን ማገልገል በሚል ሰበብ ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት ምን ያዳግታቸዋል?

Saturday, 3 November 2012
በሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርት ከተቋረጠ ከሁለት ወራት በላይ ኾኖታል
የስድሳ ዓመት ዕድሜ ባስቆጠረ ሥርዐተ ትምህርት ወደ ኮሌጅ ደረጃ አድጓል የተባለው ተቋሙ “የዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር ዝግጅት አጠናቀናል” ብሏል፤
ደቀ መዛሙርቱ በበኩላቸው “ሥርዐተ ትምህርቱ አልተለወጠም፤ ኮሌጁም አላደገም፤ ቦታው አልሚ አላገኘም” እያሉ ነው፤
ደቀ መዛሙርቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው
የኮሌጁ ዋና ዲን ቀሲስ በላይ መኰንን ለፕሮቴስታንቱ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም÷ “ዘመነ ማቴዎስ የተጠሩበት[ን] ሐዋርያዊ አገልግሎት የበለጠ የሚፈጽሙበትና የሚያስፈጽሙበት ዘመን እንዲኾንልዎ ምኞቴን ስገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው፤” በማለት በኮሌጁ የፕሮቶኮል ደብዳቤ የመልካም ምኞት መግለጫ ጽፈውላቸዋል፤ /ሰነዱን ይመልከቱ/፡፡
Friday, 2 November 2012
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ መግለጫም በማውጣት ተጠናቀቀ
- ምልአተ ጉባኤው የዕርቀ ሰላሙንአምስት የመነጋገሪያ ነጥቦች ለይቷል፤
- ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባን፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትን ይመራሉ፤
- “የመነኰሳት መተዳደሪያ ደንብ” ይወጣል፤ የገዳማት ተወካዮች በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉና ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤
- ለአኵስም ጽዮን ማርያም አዲስ ንቡረእድ ይሾማል፤
- ለካህናት ማሠልጠኛ፣ ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች (ብር 10 ሚልዮን+) እና ለሌሎችም የልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ከብር 128 ሚልዮን በላይ በጀት ተመድቧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 21/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 31/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ላለፉት ዐሥር ቀናት በሥራ ላይ የቆየው የጥቅምት 2005 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ፣ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ላይ መግለጫ ተጠናቀቀ፡፡ በ“ልዩ ልዩ ጉዳዮች” አጀንዳዎች ሥር በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰውና የበጀት ምደባን ጨምሮ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቀደም ሲል ውሳኔ ያሳለፈባቸውን የመነጋገሪያ ነጥቦች ዳግመኛ በጥልቀት ሲመለከት የቆየው ምልአተ ጉባኤው÷ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት የቅዱስ ሲኖዶሱ ልኡክ መነጋገሪያ (መደራደሪያ?) የሚያደርጋቸውን አምስት ነጥቦች መለየቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱን አቋም የሚገልጡ ናቸው የተባሉት አምስቱ ነጥቦች “የሰላምና አንድነት ጉባኤው” ላቀረባቸው ሰባት ጥያቄዎች በተሰጡ መልሶች ላይ በመመሥረት የተዘጋጁ መኾናቸውን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አስረድተዋል፡፡
ዜና ሕይወቱ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
ከደቂቀ ናቡቴ ድረ-ገጽ ላይ የተወሰደ
ልደቱ
የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ፣ መናኝ፣ ጻድቅ፣ ሊቅ፣ የሕዝብ መምህር እና የሥነ ምሕንድስና ባለሙያ የሆነው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተወለደው በ1357 ዓመተ ምሕረት በወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው ቦረና በጥንቱ ወለቃ ወረዳ ሸግላ በተባለ ቦታ ነው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እናቱ እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ስለ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ሁለት የተለያዩ ታሪኮች ይተረካሉ፡፡ የሰኔ ድርሳነ ዑራኤል ምንባብ አባቱ በመጀመሪያ የትግራይ በማስከተል የሰግላ /ጋሥጫ/ አገር ገዢ እንደነበር ይወሳል፡፡ ገድሉ ደግሞ /ጠቢብ ወማእምረ መጻሕፍት ወአቡሁኒ መፍቀሬ እግዚአብሔር አምኁልቈ ካህናተ ደብተራ ዘውሳጤ ዓጸደ ቤተ ንጉሥ/ አባቱም የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን /ሥዕል ቤት/ ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ነበረ ይላል፡፡ እንደ ገድሉ ገጸ ምንባብ ትርጉም ሕዝበ ጽዮን ከንጉሡ ሥዕል ቤት በቅዳሴ ወይም በማሕሌት ከሚያገለግሉ ካህናት አንዱ ነው፡፡ /. . . ወእሙኒ እም ሥዩማነ ወለቃ/ እናቱም ከወለቃ ሹማምንት ወገን ነች ይላታል፡፡ ይኸውም የጥንቱ ወለቃ /የዛሬው ደቡብ ወሎ፣ ቦረና ከላላ/ ከነበሩ መኳንንት ወገን መሆኗን ያመለክታል፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ወላጆች ልጅ ሳይወልዱ ለረጅም ዓመታት ቆይተዋል፡፡ የልጅ ፍላጎታቸው እንዲሠምር ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሳሉ፡፡ ስእለታቸውም ሥምሮ በመልአኩ ቀዱስ ዑራኤል አብሣሪነት ወንድ ልጅ ወለዱ፡፡ ልጃቸውን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመማጸን ስለወለዱ ስሙን ጊዮርጊስ ብለው ጠሩት፡፡ ወላጆቹ የታላቁን ሰማዕት ስም ለልጃቸው ያወጡት ወደ ፊት በዓላውያን ነገሥታት ፊት ምስክር፣ አፅራረ አምነትን አሳፋሪ፣ ካህናትንና ምእመናት በየዘመናቱ ከሚነፍሱ የኑፋቄና የክህደት ነፋሳት በወንጌል ብርሃን ነፃ የሚያወጣ ሲሉ ይህን ስም እንዳወጡለት ድርሳነ ዑራኤል እንዲህ ይተርካል፡፡ ‹‹ዘይከውን መምህረ ኵሉ ዓለም ወበጸሎቱ ዘያድኅን አሞተ ሲኦል ፍቁረ ድንግል ማርያም ወላዲቱ ለአማኑኤል፡፡ ወመገሥጾሙ ለነገሥት፡፡ ወፀሮሙ ለዐላውያን ሃይማኖት በሰይፈ ቃሎሙ ለሐዋርያት ዘያጠፍኦሙ እም ብሔረ ኢትዮጵያ፤ ወለካህናተ ጽድቅ ዘይመርሆሙ እምጽልመተ ኑፋቄ መንገለ ብርሃን ቃለ ወንጌሉ ለክርስቶስ በትምህርተ ሕጎሙ ለሐዋርያት›› ይላል፡፡
ትምህርት :-አባ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ መንፈሳዊ ትምህርቱን ከወላጅ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እንደተማረ ይገመታል፡፡ አባቱ የመጀመሪያ ደረጃ ተምህርቱን ካስተማሩት በኋላ መዐርገ ዲቁና እንዲቀበል ማድረጋቸውን ገድሉ ይነግረናል፡፡ ወሶበ ልህቀ ሕቀ ወሰዶ ኀበ ጳጳስ ወሴሞ ዲያቆነ፡፡ ባደገም ጊዜ ከጳጳስ ዘንድ ወሰደው ጳጳሱም በዲቁና አሾመው ይላል ገድሉ፡፡ ዲቁና መቀበሉን እንዲ መዓርገ ዲቁና የሰጡትን ጳጳስ ስም አይገልጽም፡፡ ዳሩ ግን መዓርገ ዲቁናን በ1341 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እስከ ዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ አካባቢ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ መተርጉም እንደተቀበለ ይገመታል፡፡
Monday, 29 October 2012
የቅ/ሲኖዶስ የቅዳሜ ውሎና ውሳኔዎች፤ ስብሰባው አልተጠናቀቀም
ቤተ ክህነታችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአጭር እና የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅድያዘጋጃል፤
ለአዳሪ እና አብነት ት/ቤቶች ማጠናከርያ 10 ሚልዮን ብር በጀት ተመድቧል፤
የካህናት ማሠልጠኛዎች በየክልሉ ይቋቋማሉ፤ በየቋንቋዎቹ የመጽሔቶችና ጋዜጦች ኅትመት ይጀመራል፤
የሥርዐተ ምንኵስና አፈጻጸም በየገዳማቱ ሕግ መሠረት ጠብቆ “ልማት እንዲጠናከርባቸው” ይደረጋል፤
የጋዜጠኛ መ/ር ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር “ብፁዓን እነማን ናቸው?” መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብበት ተወስኗል፤
የአቡነ ጳውሎስ “ንብረት” ተሰብስቦ ወደ ሙዝየም እንዲገባ ተወስኗል፡፡ ሐውልታቸውስ?
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ጸሐፊ የኾኑትን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን ከሥልጣነ ክህነት በማገድ የወሰዱት ርምጃ “በግል ጥላቻ የተገፋ ነው”ያለው ምልአተ ጉባኤው ካህኑም ሊቀ ጳጳሱም ለዕርቀ ሰላሙ በሚያመሩት ብፁዓን አባቶች አቀራራቢነት ተነጋግረው መፍትሔ እንዲሹ ትእዛዝ ሰጠ
በሕገ ወጡ የዋሽግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ላይ አስቀድሞ የተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ “የጽ/ቤቱ ባለሙሉ ሥልጣን” በሚል በአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ተሹሞ የነበረው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከተሰጠው ሓላፊነት ተወግዶ በቃለ ዐዋዲው መሠረት አዲስ ሥራ አስኪያጅ እንዲሾም ተወስኗል
በሕገ ወጡ የዋሽግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ላይ አስቀድሞ የተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ “የጽ/ቤቱ ባለሙሉ ሥልጣን” በሚል በአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ተሹሞ የነበረው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከተሰጠው ሓላፊነት ተወግዶ በቃለ ዐዋዲው መሠረት አዲስ ሥራ አስኪያጅ እንዲሾም ተወስኗል
የአቡነ መቃርዮስ የኤርትራ ጉብኝት እንደማይወክላቸው በስደት የሚገኙት አባቶች ገለጹ፤
በድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የሀ/ስብከቱን የአስተዳደር ችግር የሚያጠራው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ልኡክ ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡
Sunday, 28 October 2012
የፓትርያርክ ምርጫ ሕግን በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶሱ በኅዳር ወር መጨረሻ ልዩ ስብሰባ ይጠራል
አርእስተ ጉዳይ፡-
- READ THIS ARTICLE IN PDF
- የግብጹ ፓትርያርክ ምርጫ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደ ካይሮ ያመራል፤ በምርጫው ይሳተፋል፤
- የጠ/ቤ/ክህነቱ ‹የጨለማ ቡድን› የተቋማዊ ለውጡን አመራር ለመቀልበስ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ፤
- በወኅኒ ቤት የሚገኙ መነኰሳት ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ኾኗል፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው ከ70 ያላነሱ ‹መነኰሳት› ይገኛሉ፤
- ገዳማት የመነኮሳታቸውን ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎቻቸውን ለአህጉረ ስብከትያሳውቃሉ፤ መነኰሳት መታወቂያ እንዲኖራቸውና ከቦታ ወደ ቦታም ያለደብዳቤ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል፤
- ከአብነት ት/ቤቶች ጋራ የተያያዘው የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት ክትትል ይካሄድበታል፤ የአብነት ትምህርት መለኪያ ተበጅቶለትና በየቋንቋው መምህራን ተመድበው መምህራን በየጊዜው የሚስመርቋቸው ደቀ መዛሙርት በምደባ በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዲመደቡ ይደረጋል፤
- ምልአተ ጉባኤው በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያጣራው ልኡክ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲያመራ አዘዘ፤ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ስም በማጥፋት የኮሚቴውን ተልእኮ የሚያደናቅፉ ሕገ ወጥ ቡድኖችን እያደራጁ ነው፤
- የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤
የቅ/ሲኖዶስ የሰሞኑ ውሎ ሪፖርታዥ
- በግብጹ የፓትርያርክ ምርጫ ቤተ ክርስቲያናችን በአምስት ብፁዓን አባቶች ትወከላለች
- የጠ/ቤ/ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያ እንዲጠና ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ሰጠ::
- የውጭ ግንኙነት መምሪያ በክፍለ አህጉር ዴስኮች ይደራጃል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚዳስስ መጽሔት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይጀምራል::
- “አዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት መከፈሉ አስተዳደራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ይቀርፋል፡፡” /የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/
- ሢመተ ፓትርያርክ በምርጫ ወይስ በዕጣ? ከግብጽ ምን እንማራለን?
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 16/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 26/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 25 ቀን 2005 (እ.አ.አ ኖቬምበር 4 ቀን 2012) በሚካሄደው የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 118ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚገኙ አምስት ብፁዓን አባቶችን በልኡክነት መሠየሙን የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ አስታወቀ፡፡
Thursday, 25 October 2012
የዕርቀ ሰላሙ ውይይት በመጪው ኅዳር ወር ይቀጥላል
- ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ወሰነ፤
- እስከ መጪው ግንቦት ወር የአራቱን አህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ይቆያል፤
- የአራት ኪሎውን መንትዮች ሕንጻ ጨምሮ 283 ቤቶችንና ሕንጻዎችን ማስመለስ በሚቻልበት ኹኔታ ላይ ከከተማው ከንቲባ ጋራ ውይይት ተካሄደ።
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 15/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 25/2012/ READ NEWS IN PDF)፦ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የተመጀረው የዕርቀ ሰላም ውይይት በመጪው ኅዳር ወር መጨረሻ እንዲቀጥል ወሰነ፡፡ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ለሚቀጥለው ውይይት ምልአተ ጉባኤው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማን በልኡክነት የሠየመ ሲኾን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በልኡካን ቡድኑ ጸሐፊነት ብቻ እንዲያገለግሉ ተወስኗል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)