(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 6/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 16/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አንድነት አስፈላጊነት ከምንም በላይ በሁሉም ዘንድ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ነው። በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም “አንድነት፣ እርቅ” የሚሉት ቃላት ተደጋግመው በመሰማት ላይ ናቸው። የቀጣዩ ፓትርያርኩ ጉዳይ ከእርቅ እና ከአንድነት በኋላ እንጂ በችኮላ አሁን መሆን እንደሌለበት አጽንዖት እየተሰጠው ባለው በአሁኑ ወቅት የየራሳቸውን ወገን “ፓትርያርክ” አድርገው ለማስሾም ፍላጎት አላቸው የተለያዩ አካላት፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና ስብስቦች በይፋ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ከመንግሥት እንጀምር።
Tuesday, 16 October 2012
Monday, 15 October 2012
ዐቃቤ መንበሩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት አደረጉ

ከተሀድሶያውያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አባ ናትናኤል በወንጀል ተከሰሱ

(አንድ አድርገን ጥቅምት 5 2005 ዓ.ም)፡- ባለፈው ዓመት የሀዋሳን ህዝብ ሲያስለቅሱት የነበሩት ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ከቤተክህነት ተሾሙው እንደነበር በጊዜው ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ነገር ግን ህዝቡ እኝን አባት አስተዳዳሪ አድርገን አንቀበልም ብሎ እሳቸው በእግራቸው ቢመጡም በኮንትራት ታክሲ ከቤተክርስቲያን አባሯቸው ነበር ፤ በፊት በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት አራማጆች (ተስፋኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው ) ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን አውደ ምህረት እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙን የሚይዙ ሰው ናቸው ፡፡ በጊዜው ገንዘብ አይናቸውን አሳውሯቸው ፤ ለአውደምህረት የማይመጥኑ ፤ ትምህርቱ የሌላቸው ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ካደረኩ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡
Friday, 12 October 2012
የቃለ ዓዋዲው ማሻሻያ ረቂቅ ይመከርበት!
መስከረም 30 ቀን 2005
ሰበካ ጉባኤ በካህናትና በምእመናን ኅብረት ላይ የቆመ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ሥርዐት ነው፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሉት መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በየደረጃው አመራር ይሰጣል፣ |
መስኪድ የሚያሰሩት ሚኒስትር
- አቶ ጁነዲን ሳዶ በእናታቸው ግቢ በአርሲ ሁሩታ አርብ ገበያ አካባቢ መስኪድ እያሰሩ ነበር

Tuesday, 9 October 2012
ዋልድባን ለመታደግ በዋሽንግተን ዲሲ ትላንት ጉባኤ ተደረገ፣ ይበል የሚያሰኙ እንቅስቃሴዎችም ተደርገዋል
በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በትላንትናው ዕለት መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች አንድነት (ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ዋሽንግተን ዲሲ ንዑስ ክፍል) አስተባባሪነት የተጠራው ጉባኤ ተካሂዶ ውሏል። በጉባኤውም ላይ ካህናት አባቶች፣ ሰባኬ ወንጌል፣ እንዲሁም በርካታ ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው በመጡ የጉባኤው ታዳሚዎች በተገኙበት በርካታ ቁም ነገሮችን ተነጋግሮ እና ጉባኤው ተጠቃሏል። በቀጣይነትም ሥራዎችን በእቅድ ይዞ ለመሥራት ብሎም በአባባቢው የሚገኙትንም መዕመናን እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን በማስተባበር ለሥራ የተነሳሱ ካህናትን፣ መምህራንን፣ ዘማሪያንን፣ በትውልድ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በምዕራቡ አለም በተለያየ ሀላፊነት ላይ ያሉትን ምሁራንን እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በማስተባበር የዋልድባ ገዳም መፍረስ ሳይሆን አፈሯ እንኳን እንዳትነካ (ሳትነካ) ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ቁርጠኝነት ያሳዩበት እና በብዙ ሃዘንም እየደረሰ ያለውን እንግልት በተለያየ መልኩ ለማሳየት ተሞክሯል።
Wednesday, 26 September 2012
Thursday, 20 September 2012
እናቁም?
አንዳንዴ የትግላችን፣የጥረታችን፣የልፋታችን ውጤት መና የቀረ የሚመስልበት ጊዜ አለ፡፡ ውኃ አልቋጥር፣ ጠብ አልል ሲልብን፤ መንገዱ ሁሉ ረዥም፣ በሮቹ ሁሉ ዝግ፣ ጩኸቱ ሁሉ ሰሚ አልባ ሲመስለን፣ በመጨረሻ የምንወሰደው መፍትሔ ነገር ዓለሙን ሁሉ መተውና መሸነፍ ይሆናል፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አበቃ›› ማለት እንጀምራለን፡፡ እንኳን እኛ ቀርቶ ሌሎች እንኳን እንዳይበረቱ ‹‹ባክህ እኛም ብለነው ብለነው አቅቶን ነው›› እያልን ተስፋ እናስቆርጣቸዋለን፡፡ግን ሰው መልፋት ያለበት፣ መትጋትስ ያለበት፣ መታገልስ ያለበት፣ መሮጥስ ያለበት እስከ የት ነው?ሰው ተስፋ መቁረጥ ያለበት የት ደረጃ ሲደርስ ነው? የመንገድ ማለቂያው የት ነው? ውጤቱን ዛሬ ያላየነው ነገር ሁሉ ውጤት አልባ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላልን? በታሰበው ጊዜ ያልተደረሰበት ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይችል ነገር ነው ማለት ነው? መንገዱስ ይሄ እኛ የያዝነው መንገድ ብቻ ነውን? በሌላ መንገድስ ሊሞከር አይቻልምን?መሆኑ ከማቆምና ከመቀጠል የትኛው ይመረጣል? ከማቆም ምን ይገኛል? ከተስፋ መቁረጥ በቀር፡፡ የሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡ የቆመ ሰው ግን እንኳን ወደሚፈልግበት ለመሄድ ወደ ተነሣበት ቦታም ተመልሶ አይደርስም፡፡ የሚታገል ሰው አንድ ቀን ያሸንፋል፤ ያቆመ ሰው ግን ሳይማረክ እጁን ሰጥቷል፡፡ ደጋግሞ የሚያንኳኳ ሰው ከተኙት ሰዎች አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም፤ ማንኳኳት ያቆመው ግን እንኳን ሊቀሰቅስ ራሱም ይተኛል፡፡ የሚሄድ መኪና ጋራጅ ይደርሳል፤ የቆመ መኪና ግን ባለበት ይወላልቃል፡፡ ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡ሁለት ዕንቁራሪቶች እየተጓዙ ነበር፡፡ አንዷ ወፍራም ሌላዋም ቀጭን ነበሩ፡፡ እንዳጋጣሚ በገረወይና የተሞላ ወተት አገኙና ሰፍ ብለው ገቡበት፡፡ እዚያም አስኪበቃቸው ጠጡና ሲጠግቡ መውጣት ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ውስጡ ያንዳልጥ ስለ ነበር ለመውጣት አልቻሉም፡፡ እግራቸውን ባንቀሳቀሱ ቁጥር ወተቱ እያንዳለጠ እዚያው ይጨምራቸዋል፡፡ ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ እጅግ ደከሙ፤ ነገር ግን ከድካም በቀር ያተረፉት ትርፍ አልነበረም፡፡በምን ቀን ነው እዚህ ወተት ውስጥ የገባነው? እያሉ ቀናቸውን የሚያማርሩበት ሰዓት ላይ ደረሱ፡፡
Friday, 14 September 2012
Thursday, 13 September 2012
"የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል" ቅ/ሲኖዶስ አስታወቀ
Posted by DejeS ZeTewahedo
- “የሃይማኖት መሪዎች ጊዜ ሳያልፍ አንድነታቸውን እንዲያጠነክሩ ጸሎቴ ነው” /ፕ/ር ኤፍሬም ይሥሐቅ/
- ከመጪው ግንቦት በፊት የሚፈጸም የፓትርያርክ ሹመት እንደማይኖር እየተነገረ ነው::
- ማኅበረ ቅዱሳን ስለዕርቀ ሰላሙ ያለውን አቋም በግልጽ ዐውጆ ሂደቱን እንዲያግዝ ተጠይቋል::
- “በአሐቲ ቤተ ክርስቲያን መርሕ የቤተ ክርስቲያን ፍጹም አንድነትና ሰላም እንዲጠበቅ እንሠራለን” /የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር/::

(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 2/2004 ዓ.ም፤ September 12/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅርቡ በመንግሥት በኩል ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው የአመራር ሽግግርና የሚተካው ርእሰ መንግሥት ከተለወጠው ዘመንና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኅልፈት ጋራ ተያይዞ ከታየው የሕዝብ ጨዋነት፣ ይቅር ባይነትና ርኅራኄ አኳያ የሚመጥኑ ተፈላጊ ለውጦችን ለማምጣት የሚያስችል እንዲኾን እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክህነቱም በኩል ከቀጣዩ ርእሰ አበው ሹመት አስቀድሞ መከናወን ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ እየተገለጸ ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፓትርያርኩ ኅልፈት ተገቢውን ሰው መተካትና የተፈጠረውን ክፍተት ማሟላት ሕገ መንግሥታዊ እና ሕገ ቤተ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ በግዴታው አፈጻጸም ሂደት የሚታየው የመንግሥት ይኹን የቤተ ክህነት ባሕርይና ብቃት ለየራሱ ከጎሰኛነትና ጥቅመኛነት በላይ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንን በማስቀደም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)