Friday, 13 July 2012


የኦርቶዶክሳውያንና የጨለማው ቡድን ትንቅንቅ ከቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ስብሰባ ማግስት እስከ በዓለ ሢመት

  •   ፓትሪያሪኩ በአራት የቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነባቸው አጀንዳ ቃለጉባኤ በብዙ ጫናዎች ባለፈው ሳምንት ፈረመዋል፡፡
  •  ቋሚ ሲኖዶስ ፓትሪያሪኩ በአጀንዳዎቹ ላይ ካለመፈረማቸው ጋር ተያይዞ የቅዱሰ ሲኖዶስ የበላይነት አምነው ስላልተቀበሉና ለውሳኔዎቹ ተገዥ ስላልሆኑ  ከቅዱስነታቸው ጋር መሰብስብ እንደማይችሉ በመግለጽ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አልተሰበሰቡም፡፡
  •  “ጉባኤ አርድእት ዘተዋህዶ”  አባላት እርስ በእርሳቸው ተከፋፍለዋል፡፡ ቡድኑም በጠቅላይ ቤተክህነት እንዳይሰባሰብ ታግድዋል፡፡ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኅላፊዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቃውሞ እንዲሁም የመንግስት ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ቡድኑ ፓትሪያሪኩ አግደወታል፡፡
  •  እገዳው በጠቅላይ ቤተክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎቱ ደብዳቤ እንደሚጸና እየተጠበቀ ነው
  •  በዓለ ሢመት ጠንካራና ተጽእኖ ፈጣሪ አባቶች እንደማይገኙ በማሰብ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት የጠነሰሱትን ሴራ ለማክሸፍ ብጹአን ሊቃነጳጳሳት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
  •  ምንደኛው ኃ/ጊየርጊስ ጥላሁን በጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥአስኪያጅ አቶ ተስፋየ ውብሸት ብርቱ ትግል አቡነ ጳውሎስ መኪናው እንዲነጠቅ አድርገዋል፡፡
  • ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተመስርቷል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለመስራች ጉባኤው የምግብ ወጭ 35,000 ብር ስፖንሰር አድርጓል፡፡ 
  •  “የመለስ አባት ነው ትሉኛላችሁ፤ አዎ የመለስ አባት ነኝ” አቡነ ጳውሎስ       
  •  ማኅበረቅዱሳን በመላው ዓለም ፳ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ እያከበረ ነው



አባ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

አባ ሙሴ ጸሊም በትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አስቀድሞ በውንብድና ኑሮ ሕይወቱን ይገፋ ነበር፡፡ ሰዎች ከገድሉ የተነሳ ያደንቁታል፡፡እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ ፤ በሥራውም ኃይለኛ ነበር፡፡
አባ ሙሴ ጸሊምም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ፤ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ፡፡ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር ፡፡

አባ ሙሴ ጸሊም  ኢትዮጵያዊ

በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኮሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ፤ ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው፡፡  ያንጊዜም ተነሳ ሰይፉንም ታጥቆ ወደአስቄጥስ ገዳም ሄደ ፤ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው ፤ አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው ፡፡ አባ ኤስድሮስም ወደአባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው፡፡ እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው ታግሰህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ
የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኮሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙ እና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ፡፡፡፡በኋላም በገዳመ አስቄጥስ የገዳሙ አበምኔት የነበረው የአባ ኤስድሮስ ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ በአባ መቃርዮስ ምክር ወደ ጴጥራ ሂዶ በተባሕትዎ መኖር ቀጠለ፡፡ ከገድሉ ብዛት የተነሳ አረጋውያን መነኮሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውሃ መቅጃዎቹን ወስዶ ውሃ ሞልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር፡፡ ውሃው ከእነርሱ ሩቅ ነበርና እንዲህም እያደረገ በመጋደል ለብዙ ዘመናት ኖረ ፡፡
አባ ሙሴ ጸሊም በበአቱ እያለ የፈቲው ፆር ያሠቃየው ነበር፡፡ ፈተናውን ተቋቁሞ በበአቱ መቀመጥ ስላልቻለ ወደ ገዳሙ አበምኔት ወደ አባ ኤስድሮስ ዘንድ ሄደና ‹በበኣቴ መቀመጥ አልቻልኩም› አለው፡፡ አባ ኤስድሮስም ወደ በኣቱ ተመልሶ በዚያው እንዲጸና መከረው፡፡ ሙሴ ግን ‹ፈጽሞ አልችልም› አለ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ኤስድሮስ ሙሴን ይዞት ከገዳሙ ቅጥር ውጭ አወጣው ከዚያም ወደ ምዕራብ አዞረውና ‹ተመልከት› አለው፡፡ በዚያ አቅጣጫ የአጋንንት መንጋ ለወረራ ሲዘጋጁና ሲንጫጩ አሳየው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ምሥራቅ እንዲመለከት አደረገውና እልፍ አእላፍ መላእክት ብርሃን ተጐናጽፈው አሳየው፡፡ ከዚያም ‹እነዚህ የብርሃን መላእክት ቅዱሳንን ለመርዳት ከእግዚአብሔር የሚላኩ ናቸው እነዚህ ርኩሳን አጋንንት ደግሞ ቅዱሳንን ለመፈተን የሚዘምቱ ናቸው፡፡ የብርሃን መላእክት ኃይል ከአጋንንት ኃይል ይበልጣሉና ጸንተህ ተጋደል› ሲል መከረው አባ ሙሴም ወደ በኣቱ ተመለሰ፡፡
አባ ሙሴ በገዳመ አስቄጥስ እያለ ከገዳማውያን አንዱ ጥፋት ሠራና ማኅበሩ ለፍርድ  ተሰበሰበ፡፡ አባ ሙሴ ግን በጉባኤው ላይ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ካህኑ ተልኰ ‹ና. ሁላችንም አንተን እየጠበቅን ነው› አለው፡፡ አባ ሙሴም በሚያፈስስ ከረጢት አሸዋ ሞልቶ ያንንም በጀርባው ተሸክሞ ከኋላው እያፈሰሰ ወደ ጉባኤው አመራ፡፡ ጉባኤተኞቹ ተገርመው ለምን እንደዚህ እንዳደረገ ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹የእኔ ኃጢአቶች በኋላየ እንደዚህ አሸዋ በዝተው ይፈሳሉ፤ ነገር ግን ላያቸው አልቻልኩም ዛሬ ግን በሌላው ላይ ለመፍረድ መጥቻለሁ፡፡› አላቸው፡፡ ይህን ሲሰሙ ዝም አሉ፡፡ ያን ወንድምም በይቅርታ አለፉት፡፡
በሌላ ጊዜ በገዳመ አስቄጥስ ያሉ መነኰሳት ተሰበሰቡና የአባ ሙሴን ትዕግሥት ለመፈተን ሲሉ “ይህ ጥቁር መነኩሴ ለምን እዚህ መጣ “ ብለው ተናገሩት፡፡ እርሱም ዝም አለ፡፡ ጉባኤው ሲበተን “አባ ክፉ ስንናገርህ ምንም ሐዘን አልተሰማህም ነበርን ?” ሲሉ ጠየቁት፡፡ “ተሰምቶኛል፣ ነገር ግን እንዳልናገረው አንደበቴን ተቆጣጠርኩት” አላቸው፡፡
በአንድ ወቅት በገዳመ አስቄጥስ ጾም ታወጀ፡፡ በዚያ ሳምንት አባ ሙሴን ለማየት ከግብጽ ወንድሞች መጡ፡፡ አባ ሙሴም በእንግድነት ተቀበላቸውና ምግብ ያበስልላቸው ጀመር፡፡ የእሳቱን ጢስ የተመለከቱ ጐረቤቶቹ “አባ ሙሴ ትእዛዝ አፍርሶ ምግብ ያበስላል” ብለው ለገዳሙ ሓላፊዎች ተናገሩ፡፡ ሓላፊዎቹም ‹አሁን ተውት ሲመጣ እኛው ራሳችን እናናግረዋለን› አሏቸው፡፡ ሓላፊዎቹም አባ ሙሴን ጠርተው ለምን ምግብን እንዳበሰለ ተረዱ፡፡ በቀዳሚት ሰንበት ማኅበሩ ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ በአደባባይ ‹አባ ሙሴ ሆይ የሰውን ትእዛዝ አልጠበቅኽም፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ (እንግዳ ሆኜ መጥቼ ተቀብላችሁኛል የሚለውን) ግን ጠብቀሃል› ብለው አመሰገኑት፡፡
አንድ ጊዜ የአካባቢው ገዥ ስለ አባ ሙሴ ዝና ሰምቶ ያየው ዘንድ ወደ ገዳመ አስቄጥስ መጣ፡፡ ይህን የሰማው አባ ሙሴ ሸሽቶ ወደ ጫካ ገባ፡፡ በመንገድም ላይ የገዥው መልእክተኞች አገኙትና ‹እባክህ አባ ሙሴ የት እንዳለ በኣቱን አሳየን› አሉት፡፡ ‹ከርሱ ምን ትሻላችሁ፤ እርሱ ኮ ቂላቂል ነው› አላቸው፡፡ ይህን የሰማው የአካባቢው ገዥ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጣና የሆነውን ሁሉ ለአገልጋዮች ነገራቸው፡፡ ‹ብዙ ሰዎች ስለ አባ ሙሴ ሲያወሩ ሰምቼ ለማግኘት መጥቼ ነበር፤ በመንገድ ላይ ያገኘነው አንድ አረጋዊ ሰው ግን የአባ ሙሴ በኣት የት እንደሆነ ስንጠይቀው ከርሱ ምን ትሻላችሁ እርሱ ኮ ቂላቂል ነው አለን› ብሎ ነገራቸው፡፡ አገልጋዮቹም በጣም ተናደዱና ‹ምን ዓይነት አረጋዊ ሰው ነው ስለ ቅዱሱ ይህን የሚናገር› ብለው ጠየቁት፡፡ ‹ትልቅ፣ ጠቆር ያለ፣ አሮጌ ልብስ የለበሰ ነው› አላቸው፡፡ አገልጋዮቹም ተገርመው ‹ይህማ ራሱ አባ ሙሴ ነው፤ ይህን ያለህ ሊያገኝህ ስላልፈለገ ነው› አሉት፡፡ የአካባቢው ገዥም ከአባ ሙሴ ሁኔታ ከንቱ ውዳሴን ስለ መሸሽ ትልቅ ትምህርት ተምሮ ተመለሰ፡፡
አባ ሙሴ በኣት ሠርቶ ወደ ጴጥራ ሲሄድ በአካባቢው ውኃ ስላልነበረ ተጨንቆ ነበር፡፡ አንድ ድምፅ ‹ሂድ ስለምንም ነገር አትጨነቅ› አለው፡፡ ስለዚህም በዚያ መኖር ጀመረ፡፡ አንድ ቀን በጴጥራ እያለ አበው ሊጐበኙት መጡ፡፡ የነበረችው ውኃ ጥቂት ነበረችና በርሷ ምግባቸውን አበሰለ፡፡ የሚያጠጣቸው ግን አላገኘም፡፡ ስለዚህ ወደ ውጭ እየወጣ ውኃ ይሰጠው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በመጨረሻ ዝናብ ዘነበና የውኃ ማጠራቀሚያዎቹን ሁሉ ሞላቸው፡፡ እነዚያ አባቶችም ‹ትወጣና ትገባ የነበረው ለምን እንደሆነ እባክህ ንገረን› አሉት፡፡ ‹እናንተ በእንግድነት ስትመጡ ውኃ አልነበረኝም፣ ስለዚህ ያንተን አገልጋዮች ወደ እኔ ልከሃቸዋል፣ ነገር ግን ውኃ የለኝም፣ ስለዚህ እባክህ ውኃ ስጠኝ እያልኩ እግዚአብሔርን ለመለመን ነበር› አላቸው፡፡

 አንድ ወንድም አባ ሙሴን ‹አንድን አገልጋይ ባጠፋው ጥፋት የተነሣ ጌታው መታው፡፡ አገልጋዩ ምን ማለት አለበት?› ብሎ ጠየቀው፡፡ አባ ሙሴም ‹አገልጋዩ ብፁዕ ከሆነ፣ አጥፍቻለሁና ይቅር በለኝ ማለት አለበት፡፡› አለው፡፡ ‹ሌላ አይጠበቅበትምን?› ሲል ያ ወንድም ጠየቀው፡፡ ‹አይጠበቅበትም፣ ለጊዜው ለጥፋቱ ሓላፊነቱን ወስዶ አጥፍቻለሁ ካለ ጌታው ይቅር ይለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ዓለማው በባልጀራ ላይ ላለመፍረድ ነው፡፡ በእውነቱ ጌታችን የግብጽን በኩራት ሁሉ ሲመታ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት አልነበረም› አለና መለሰለት፡፡ ያም ወንድም ‹ምን ማለት ነው?› አለው፡፡ ‹ሁላችንም የየራሳችንን ጥፋቶች ካየን የባልንጀራችንን ለማየት ዕድል አንሰጥም፡፡ በራሱ ቤት ሰው የሞተበት በጐረቤቱ ልቅሶ ለማልቀስ አይሄድም፡፡ ለባልንጀራ መሞት ማለት ለራስ ጥፋት ትኩረት በመስጠት፣ የሌላውን ጥፋት ከቁም ነገር አለመቁጠር ነው፡፡ ማንንም አትጉዳ፣ በማንም ላይ ክፉ አታስብ፣ ክፉ የሚሠራውን ሰው አትናቀው፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ በሚሠራ ሰው ላይ አትተማመን፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ ከሚሠራ ሰው ጋር አትደሰት፣ ለባልንጀራ መዋቲ መሆን ማለት ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ አትማረር፣ ነገር ግን ‹ሁሉንም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡› በል፡፡ ከሚያማ ሰው ጋር አትተባበር፣ በሐሜቱም አትደሰት፣ ወንድሙን የሚያማውን ሰውም አትጸየፈው፡፡ አትፍረድ ማለት ትርጉሙ ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ የጥላቻ ሓሳብ አይኑርህ፣ ጥላቻ ልብህን እንዲያሸንፈውም አትፍቀድለት፡፡ ባልንጀራውን የሚጠላውን አትጥላው፣ ሰላም ማግኘት ማለት ይህ ነው፡፡
አንድ ጊዜ በገዳመ አስቄጥስ ወንድሞች አብረውት እያሉ አባ ሙሴ ‹ተመልከቱ በርበሮች ገዳማችንን ሊያጠፉ እየመጡ ነው፡፡ ተነሡና ሽሹ› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ‹አባ አንተስ አትሸሽምን?› ሲሉ ጠየቁት፡፡ አባ ሙሴም ‹እኔማ ይህችን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ፡፡ ጌታ በወንጌል ‹ሰይፍን የሚያነሡ በሰይፍ ይጠፋሉ› ያለው ቃል (ማቴ. 25.52) ይፈጸማል፡፡› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹እኛም አንሸሽም፣ አብረን እንሞታለን እንጂ› አሉት፡፡ አባ ሙሴም ‹ያ ለእኔ ረብ የለውም፤ ሁሉም ሰው ለየራሱ ይወስን› ብሉ መለሰላቸው፡፡ በዚያ ለነበሩት ሰባት ወንድሞች ‹በርበሮች ወደ ገዳሙ ደጅ እየደረሱ ነው› ብሎ ነገራቸው፡፡ ወዲያውም በርበሮቹ ደርሰው ገዳማውያኑን በሰይፍ መቷቸው፡፡ ከሰባቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ሸሸና በተቆለለው ሰሌን ውስጥ ተደበቀ፤ ወዲያውም ሰባት አክሊላት ሲወርዱላቸው ተመለከተ፡፡
የአባ ሙሴ ጸሊም በረከት ይደርብን አሜን
ዋቢ   ስንክሳር ሠኔ 24
በበረሓው ጉያ ውስጥ

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ


  • የደብሩ ማኅበረ ካህናት የፈረሙበትን ደብዳቤ ተመልከቱ

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

ሊቀ ጳጳሱ መግለጫዎቻቸውን እና መመሪያዎቻቸውን ጸረ ተዋሕዶ በሆኑ ብሎጎች/ የጡመራ መድረኮች ላይ ማውጣታቸውን በጽኑዕ የነቀፈው መግለጫው “የብፁዕነታቸው ማንኛውም መልዕክት ያለ እሳቸው ፈቃድ ነው የወጣው እንዳይባል ምንም ዓይነት የጽሑፍ ማስተባበያ ያልሰጡ በመሆናቸው እና ይህንና ይህንን በመሳሰሉት የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ምክንያት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማምጣት ሳይሆን መለያየት ምክንያት ከመሆናቸው በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን ክብር እና መቆርቆር እንደሌላቸው ከዚህ ተግባራቸው ተረድተናል። ስለዚህ … ቤተ ክርስቲያናችን አብራ የማትሠራ መሆኑን እና የፈፀሙትንም ተግባር የምንቃወመው መሆኑን ለሚመለከተው አካላት ሁሉ መግለፅ አስፈልጎናል። በአጠቃላይ የብፁዕነታቸው አካሄድ፦ 1. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን የዘነጋ፣ 2. የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያስቀመጡትን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀስ በቀስ የሚሸረሽር በመሆኑ … ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት የማንችል መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ለመላከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ እና ለዲ. ስዩም ወ/አረጋዊ የተሠጠውን ሹመትም የማንቀበል መሆኑን እናስታውቃለን” ይላል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።


ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

11 comments:

Anonymous said...
Endih New Enji Jegninet... Enat eko lijochuwan yemititebikibet gize new
Anonymous said...
Great Vegas,that how it should be done.Everyone should learn from vegas.
Anonymous said...
ይበል የሚያሰኝ ነዉ ቬጋሶች እንዲያ ነዉ እንጂ!

ለሌሎች አራአያነት ያለዉ ሥራ ነዉ የሠራችሁት ሌሎችም የናንተኑ ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነዉ። በተለይ ስም በመጥራት (ከመረቁ አዉጡልኝ ... አይነት) ላይ ያሉትም እንዲሁ ሊያደርጉ ይገባቸዋል። ደጋፊዎች አሉኝ እያሉ እዚያ አገር ቤት የሚያወሩትና የሚያስወሩትም ለዚሁ ይመስላል። አቡነ ፋኑኤልን ባዶአቸዉን የምናስቀርበት ጊዜ አሁን ነዉ።
አቡነ ፋኑኤል እና አቡነ ጳዉሎስ ከነ ግብር አበሮቻቸዉ የቤተ ክርስቲያናችንን እድገት ሳይሆን ዉድቀትዋን ለማየት የሚናፍቁ ናቸዉና በተለይ በዚህ በሰሜን አሜሪካ በቃችሁ ልንላቸው ይገባናል።
መቼም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያያቸዉ እንደማይፈልግ ስለሚያዉቁ ከዚህ በኅላ ወደ አገር ቤት ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳደር አይሄዱም: እዚያዉ እንደለመደባቸዉ የራሳቸዉን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክስቲያን ይዘዉ ቁጭ እንዲሉ ማድረግ ነዉ ::
Anonymous said...
Great job. All what they pointed out are acceptable.
Anonymous said...
I have been suggesting this for a long time. This is the only way to deal with Abune Paulos and his political and ethinic coronies. It is time believers fought back against, church gear clad so called fathers. It is enought they abuse poor church goers in Ethiopia, they shouldn;t be allowed to ran amock in a place we sought refugee from thier brutality. God bless
Anonymous said...
ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ውሳኔ። እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅ።
ሁላችንም የነሡን ፈለግ በመከተል በየአብያተ ክርስቲያኑ ያሉ መናፍቃንን ጥፋት እንከላከል።
Anonymous said...
Thank God! and thanks vegas here you go the real orthodox followers and keep it up.we expect more jobs like this clearing the unclean. the God of our fathers be with you.God for the sake of your mother and our holly fathers please protect our church.amen
Anonymous said...
እናታችንን የመጠበቅ ግዴታ አለብን ጐበዝ ቨጋስ ጠንካራ ክርስትያን ያለበት ብዙ ፈተና ያሳለፉ ወንድሞችና እህቶች ያሉበት ነው አሁንም ከነዚህ በተክርስትያንን ከምጠሉ ጋር ህብርት ያለው ማንም ይሁን ማን በጥንቃቄ እንድታዩት አደራ እናንተ ውስጥ እርም የሆነውን ቤቱ ያስቀመጠ አለና
Anonymous said...
ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን ቬጋሶች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ስለሃይማኖት በሰው ፊት እውነትን መመስከር ማለት ጌታችን በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ ማቴ 10፥ 32 ያለውን ምስክርነት ያገኛል በሃይማኖት ዲፕሎማሲያዊ መልስ የለም ባይሆን ከመረቁ ማለት ለቤተክርስቲያን አይደለም ለዓለምም ያሳፍራል አባ ጳውሎስ አባ መላኩ ወይም አባ ፋኑኤል እና መሰሎቻቸው የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚመኙ ብቻ ሳይሆን የቤተከረሰቲያናችንን ጥፋት የሚያፋጥኑ ናቸው እኛ ዝም ካልን ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ተዋህዶን ከኢትዮጵያ ምድር ልናጣት ተስማምተናል ማለት ነው ከናንተ መካከል ነውር የሆነውን ወደ ቤታቸው ያስገቡ አሉ ያሉ አስተያየት ሰጪ የሚያውቁትን ለመመስከር እርስዎስ ምን ያዘዎት እገሌ ወደ ቤትህ ያስገባሀውን ነውር ያውጣ ለምን አይሉም ለማንኛውም ለስልጣን ለጥቅምና ለተለያዩ ተራና አላፊ ነገሮች ስንል ቤተክርስቲያንን አሳልፈን ለምንሰጥና ለምንተባበር ወዮልን
Anonymous said...
Thanks Dejeselam....
Dn Seyoum Asfaw Teklearegay teblo Yistekakel
Dn seyoum w/agetay yemilew sihtet new
Anonymous said...
ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን ቬጋሶች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ስለሃይማኖት በሰው ፊት እውነትን መመስከር ማለት ጌታችን በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ ማቴ 10፥ 32 ያለውን ምስክርነት ያገኛል በሃይማኖት ዲፕሎማሲያዊ መልስ የለም ባይሆን ከመረቁ ማለት ለቤተክርስቲያን አይደለም ለዓለምም ያሳፍራል አባ ጳውሎስ አባ መላኩ ወይም አባ ፋኑኤል እና መሰሎቻቸው የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚመኙ ብቻ ሳይሆን የቤተከረሰቲያናችንን ጥፋት የሚያፋጥኑ ናቸው እኛ ዝም ካልን ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ተዋህዶን ከኢትዮጵያ ምድር ልናጣት ተስማምተናል ማለት ነው ከናንተ መካከል ነውር የሆነውን ወደ ቤታቸው ያስገቡ አሉ ያሉ አስተያየት ሰጪ የሚያውቁትን ለመመስከር እርስዎስ ምን ያዘዎት እገሌ ወደ ቤትህ ያስገባሀውን ነውር ያውጣ ለምን አይሉም ለማንኛውም ለስልጣን ለጥቅምና ለተለያዩ ተራና አላፊ ነገሮች ስንል ቤተክርስቲያንን አሳልፈን ለምንሰጥና ለምንተባበር ወዮልን

Wednesday, 11 July 2012

ደጀ ሰላም Deje Selam: ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰ...


ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰቡ አገደ


·         እገዳው የተላለፈው መንግሥት ለአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ነው ተብሏል።
·         በአባ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለቀናት በኅቡእ ሲሰበሰብ የቆየው ቡድኑ÷ ከፊል መሥራች አባላቱ ከሸሹትና የስብሰባ እገዳ ከተጣለበት በኋላ÷ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የ‹ዕወቀኝ› ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል።
·   የቅ/ሲኖዶስ እና የጠቅ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤቶች÷ ቤተ ክርስቲያን “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘውን ኅቡእ ቡድን እንደማታውቀው ገልጸዋል።
·     የኅቡእ ቡድኑ አስተባባሪ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ የያዘውን የጠ/ቤ/ክህነቱን መኪና እንዲያስረክብ ተደርጓል።
·   አባ ጳውሎስ የእምነት ንጽሕናቸውን በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ያላረጋገጡትንና ከቡድኑ ቀንደኛ አስተባባሪዎች አንዱ የኾኑትን አባ ሰረቀን በመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ሥ/አስኪያጅነት ለመሾም ማሰባቸው ተሰምቷል።
·    “ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ሲባል የቡድኑን ኅቡእ እንቅስቃሴ በጥብቅ እየተከታተልነው ነው” /የጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች/።
·     “ከጉባኤው አስተባባሪዎች አብዛኞቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት ያጡ ግለሰቦች ናቸው” /የቋሚ ሲኖዶስ ምንጮች/።
 (ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 4/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 11/ 2012/ READ IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” በሚል መጠሪያ ሰይሞ ከቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ አስተዳደር ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ይኹንታ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነንት ለማጠናከር፣ መንፈሳውያን ማኅበራትን ለማፈራረስ፣ የግል እና የቡድን ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ መሽጎ ሲዶልት የቆየው ቡድን በየትኛውም የመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሾች እና ቢሮዎች ለመሰብሰብ እንደማይፈቀድለት አስታወቀ፡፡


ባለፈው ሳምንት፣ ሰኔ 26 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎት ሓላፊ ሊቀ ኅሩያን ዓለም እሸት ገብረ ጻድቅ ተፈርሞ በአድራሻ ለጥበቃ አገልግሎት ክፍል የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው÷ ራሱን “ጉባኤ አርድእት” በሚል የሚጠራው ቡድን ከቅዱስ ሲኖዶስ ይኹን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተሰጠው አንዳችም ዕውቅና የለውም፤ የጉባኤው አስተባባሪዎች በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ በውል ተለይቶ ላልታወቀና ላልተፈቀደ ዓላማ በኅቡእ መሰብሰባቸው ሕገ ወጥነት በመኾኑ የትኛውንም አዳራሽ ይኹን ቢሮ ለስብሰባ መጠቀም አይችሉም፤ የጥበቃ አገልግሎት ክፍሉም ይህንኑ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ከዚህ ደብዳቤ ባሻገር “ጉባኤ አርድእት”ን የሚመለከተው የስብሰባ እገዳ በማሳሰቢያ መልክ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቅጽር በይፋ እንዲለጠፍ መደረጉ ተገልጧል፡፡

የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች ለደጀ ሰላም እንደገለጹት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባይ አስተባባሪዎች በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰቡ የሚያግዳቸው ውሳኔ የተላለፈው÷ ቡድኑ ዕውቅና ባልተሰጠው ማንነቱና በሌለው ሥልጣን ፓትርያርኩ ላለፉት ሰባት ዓመታት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ሲኖዶሳዊ ባልኾነ መንገድ ለመለወጥ በተለያየ መንገድ የሚያደርጉትን ሙከራ በማገዝ፡- የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን እንዳሻቸው ለመሾምና ለመሻር፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ከአንዱ ሀገረ ስብከት ወደ ሌላው እንዳሻቸው ለማንከራተት፣ ኤጲስ ቆጶሳትን እንዳሻቸው ለመሾም. . . ወዘተ በማስቻል ዐምባገነናዊ አስተዳደራቸውን ለማጠናከር፤ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበርና ሌሎችም በቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት መስፋፋትና መጎልበት ዙሪያ የሚሠሩ ማኅበራትን በ”ባዕድ አደረጃጀትና ተቀጽላ” እንዲቆጠሩ በማድረግ ለማፈራረስ፤ ከዚህ ጋራ ተያይዞና ይህን ተከትሎ በሚፈጠረው ክፍተትም “ጥናትና ምርምር አደርጋለኹ፤ ቅዱስ ፓትርያርኩንና ቅዱስ ሲኖዶስን አማክራለኹ” በሚል ስም የግልና የቡድን ጥቅሙን ብሎም የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ሤራ ለማሳካት የወጠነው ዕቅድ በብዙኀን መገናኛ መጋለጡን ተከትሎ መንግሥት ለአባ ጳውሎስ በሰጠው ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መኾኑ ተገልጧል፡፡

ለ”ጉባኤ አርድእት” ነን ባይ ግለሰቦች በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩና በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይቀር የመሰብሰብ ፈቃድና ሌሎችንም ድጋፎች በመስጠት የሕገ ወጥ ዓላማቸው ተባባሪ በመኾናቸው ክፉኛ የተወቀሱት አባ ጳውሎስ÷ በቡድኑ ነውጠኛ እንቅስቃሴ ሳቢያ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚፈጠር ማንኛውም ሁከት ብቸኛ ተጠያቂው እርሳቸውና እርሳቸው ብቻ እንደሚኾኑ ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡ አባ ጳውሎስ ቡድኑ በኅቡእ ሲያካሂድ የቆየውን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ መደገፋቸውን ለማበል ሞክረው እንደነበር ምንጮቹ የጠቆሙ ሲኾን÷ ከመንግሥት በተሰጣቸው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እና “በዚህ የተነሣ በዓሌን (ነገ የሚከበረውን 20ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን) አላበላሽም” በሚል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት በሰጡት መምሪያ የስብሰባ እገዳው ደብዳቤ እንደተጻፈ ነው የተመለከተው፡፡

አባ ጳውሎስ 12 ንኡሳን ኮሚቴዎች ያቋቋሙለትንና ቀደም ሲል በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መመደቡ የተነገረውንግማሽ ሚሊዮን ብር ሳይጨምር÷ የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በሀ/ስብከቱ ጠንካራ አድባራትና ገዳማት ላይ በሚፈጥሩት አስገዳጅነትና ልዩ ልዩ ማግባቢያ እየተሰበሰበ የሚገኘው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ወጪ የሚደረግበትን የኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን “በሰላም ለማክበር” በሚል የ”ጉባኤ አርድእት” አስተባባሪዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዳይሰበሰቡ መከልከላቸው ስልታዊ እንጂ ልባዊአለመኾኑን ነው ምንጮቹ የሚናገሩት፡፡

ለዚህም የቡድኑ ዋነኛ አስተባባሪዎች (አባ ሰረቀን ጨምሮ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን፣ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ አእመረ አሸብር፣ ብርሃኔ ገብረ ጻድቃን) በተለይም የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ በኾኑት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ቢሮ መሰብሰብ መቀጠላቸውን እንደ አስረጅ ይጠቅሳሉ፡፡ አባ ጳውሎስ የቡድኑ ሤራ በብዙኀን መገናኛ በመጋለጡ ዋነኛ አስተባባሪዎቹን ‹በማኅበረ ቅዱሳን ተበልጣችኋል›በሚል ዘልፈውና አብጠልጥለው ሲያበቁ÷ አልፈርምም በሚል አሻፈረኝ ያሉበትን የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ያስተላለፈውን ቃለ ጉባኤ ዘግይተው መፈረማቸው ሌላው የተቃውሞ ማብረጃ፣ የማዘናጊያና በዓለ ሢመትን ለማድመቅ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ድጋፍ የማሰባሰብ ስልት ኾኖ ተወስዷል፡፡

ሌላው የአባ ጳውሎስን ውሳኔ ስልታዊ ነው ያሰኘው አስረጅ በበዓለ ሢመታቸው ማግስት ለአባ ሰረቀ ሕገ ወጥ ሹመት በመስጠት የተናጋውን የኀይል ማእከላቸውን ለማጠናከር ያሰቡት ዕቅድ ነው፡፡ ይኸውም የግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጥንተ አብሶን በተመለከተ÷ በእመቤታችን ክብርና ቅድስና ላይ ያላቸውን የእምነት አቋም ጉዳዩን እንዲያጣራ ለተቋቋመው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ጉባኤ ጥምር ኮሚቴ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ የተላለፈውን ውሳኔ በአግባቡ መፈጸማቸው በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ሳይረጋገጥ ጥቅምት 27 ቀን 2004 ዓ.ም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለማድረግ አስተላልፈውት የነበረውን ሕገ ወጥ ትእዛዝ ለመተግበር መወሰናቸው ነው፡፡

“በንጹሕ እምነቴ ላይ ከደረሰብኝ ከባድ የስም ማጥፋት ወንጀል ነጻ መኾኔን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይዣለኹ”በሚል በራሳቸው ጊዜ ‹ነጻነታቸውን› እያወጁ የሚገኙት አባ ሰረቀም÷ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ (ክልፍልፊት)ና እጅጋየሁ በየነ (ኤልዛቤል) አጋፋሪነት የቋመጡለትን የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሹመት ለማግኘት እየተፍጨረጨሩ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ነውር ጌጣቸው፣ ሕገ ወጥነት ልማዳቸው ለኾኑት እኒህ ሁለት ግለሰቦች የሚያስጨንቃቸው÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያን የምክትል ሥራ አስኪያጅ ሹመትን በተመለከተ በአንቀጽ 30 ንኡስ አንቀጽ 9 መሠረት÷ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሥልጣነ ክህነት፣ በቂ የትምህርት ደረጃና ችሎታ ያላቸውን ሦስት ሰዎች በዕጩነት ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቦ በማስመረጥ ቋሚው ቅ/ሲኖዶስ ሲስማማበት ብፁዕነታቸው በሚጽፉት ደብዳቤ በፓትርያርኩ እንደሚሾም የተቀመጠው ድንጋጌ መጣስ አይደለም፡፡ አባ ጳውሎስንና ነውረኞቹን እነኀይለ ጊዮርጊስን የሚያስጨንቃቸው አባ ሰረቀ÷ ለዚያውም በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት÷ የሚሾሙት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት የእምነት ንጽሕናቸው በሚመለከተው አካል ፊት አለመረጋገጡ አይደለም፡፡ የእነርሱ ስጋት ሹመቱን በቀዳሚነት በሚቃወሙት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ፊልጶስና የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ሳቢያ የበዓለ ሢመቱ አከባበር ጥላ እንዳያጠላበት ነው፡፡ ስለዚህም አባ ሰረቀን በም/ሥ/አስኪያጅነት ለማስቀመጥ የተያዘው ዕቅድ ከበዓለ ሢመቱ በኋላ እንዲኾን መታሰቡ እየተነገረ ነው፡፡

ምናልባትም በበዓለ ሢመቱ ሳቢያ በመዲናዪይቱ አዲስ አበባ የሚሰበሰቡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ ይኸው የአባ ሰረቀ ሹመት በአጀንዳ የሚቀርብላቸው ከኾነ የግንቦቱን ውሳኔ አፈጻጸም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሊጠይቁ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ በዚህም አጋጣሚ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ አባ ሰረቀ ስለእምነት ሕጸጽ የቀረበባቸውን ጥያቄ አስመልክቶ ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ጉባኤ አባላት ጥምር ኮሚቴ የሰጡትን ምላሽ በተቀመጠው ውሳኔ አግባብ በጽሑፍ ሳያረጋግጡ “ነጻነቴን አውጆልኛል” ያሉትን ደብዳቤ ወጪ ስላደረጉበትና ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት ጠንካራ ወቀሳ ስላስከተለባቸው የጫና አሠራር ማብራሪያና ይቅርታ እንደሚጠይቁ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል የ”ጉባኤ አርድእት” ነን ባይ አስተባባሪዎች በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሾችና ቢሮዎች እንዳይሰበሰቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መታገዳቸውን ተከትሎ የቡድኑ ቀንደኛ አስተባባሪ የኾነው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ከአሜሪካ ከመጣ ጀምሮ በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ የሚያሽከረክረውን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን መኪና በምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ውብሸት ትእዛዝ እንዲያስረክብ መደረጉ ታውቋል፡፡ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ በሰሜን አሜሪካ “የአህጉረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ” እና የሕገ ወጡ “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ባለሙሉ ሥልጣን” ኾኖ በአባ ጳውሎስ እብሪት ለተሾመበት ሥልጣን ያስፈልገኛል ያለው በጀት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ ተግዳሮት የገጠመው መኾኑም ተሰምቷል፡፡

“የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር” (Ethiopia Assemblies of God) በሌላ ሰበካ ስያሜው “ቤዛ ቸርች” የተሰኙትን የፕሮቴስታንት አብያተ እምነት እንደሚከታተል የተጋለጠው ፕሮቴስታንታዊ ኀይለ ጊዮርጊስ÷ መረጃው በደጀ ሰላም ይፋ ከተደረገ በኋላ ሞራላዊ ይዞታው በከፍተኛ ደረጃ ተንኮታኩቶ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡ ግለሰቡ የለየለት ፕሮቴስታንት መኾኑን የገለጸው የዜና ጥቆማ በጡመራ መድረካችን ከወጣ በኋላ የኀይለ ጊዮርጊስን ግላዊ ሕይወት ጨምሮ በሥራ አጋጣሚ በተዘዋወረባቸው አካባቢዎች በቅርበት የሚያውቁትደጀ ሰላማውያን በርካታ ማስረጃዎችን ለጡመራ መድረካችን ማድረሳቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከእኒህም መካከል ከሰሜን ወሎ - ወልዲያ፣ ከደቡብ ጎንደር - ደብረ ታቦር፣ ከምዕራብ ጎጃም - አጉንታ ማርያምና ባሕር ዳር እንዲሁም ከመዲናዪቱ አዲስ አበባ ያገኘናቸው ይጠቀሳሉ፡፡

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የሚመለከቱ ግላዊ ማስረጃዎችን እናቆያቸውና ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮጀክት አስተባባሪ ኾኖ ወልዲያ ከተማን ማእከል አድርጎ ይሠራ በነበረበት ወቅት ወጣቶችን በቤቱ ሰብስቦ እጆቹን በፕሮቴስታንታዊ ዘይቤ ጭኖ ይጸልይ፣ ይሰብክና ይዘምር እንደነበር የሚያሳየው ማስረጃ አስደናቂ ኾኖ አግኝተነዋል፡፡ በወቅቱም ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ በማኅበረ ቅዱሳን የወልዲያ ንኡስ ማእከልና በሰንበት ት/ቤቶች አባላት የተባበረ ጥረት ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ መታገዱን አረጋግጠናል፡፡

ከአዲስ አበባ የመንበረ ፓትርያርክ ምንጮቻችን ያገኘው ማስረጃ ደግሞ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ በሙስኛ ተግባራቸው ከላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት ተነሥተው ለአባ ጳውሎስ በሰጡት መተያያ (ከፍተኛ የዝውውር ክፍያ እንበለው?) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ በኾኑት አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ ሹመት ጀርባ ከባለሟላ እጅጋየሁ በየነ ጋራ ስሙ እየተነሣ መኾኑን ይጠቁማል፡፡ አባ አእምሮ ሥላሴ በ”ጉባኤ አርድእት” አባልነት በፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ እና በሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ አማካይነት አስወዳጅም አስገዳጅም በኾነ መንገድ እየተመለመሉ ከሚገኙት የሀ/ስብከቱ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ካህናት ተባባሪ አባላት መካከል አንዱ መኾናቸው የማስረጃውን እውነታ አጉልቶታል፡፡

ሞራላዊ ይዞታው ከተንኮታኮተ በኋላ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን እንደ እኵያ/ጓደኛ በመቁጠር በጽሑፍ ለመግለጽ በሚያሳፍርና ለጡመራ መድረኩ በማይመጥን አኳኋን በፍጹም ንቀትና ዘለፋ የሚናገርበት የድምፅ ማስረጃም ሌላው ጥቆማ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ጋጠ ወጥነቱ የብዙዎችን ቁጣ እያነሣሣ የሚገኘው ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ “ከመቸው ጊዜው ደርሶ በሄደልን?” በማለት አምርረው የሚናገሩ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኞች ፍጹም ጥላቻ ማትረፉን ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡ ከብዙኀኑ ፍጹም ጥላቻ የቀሩለት ባልንጀሮቹም በሰሞኑ የኮሌጅ ምረቃቸው ዕለት ከእጅጋየሁ በየነ ጋራ በፕሮቴስታንታዊ ዳንኪራ ያስረገጡት መናፍቁ አሰግድ ሣህሉና አእመረ አሸብር (ከ”ጉባኤ አርድእት” ሌሎች አመራሮች ጋራ) መኾናቸው ተገልጧል፡፡

ከአባ ጳውሎስ ባገኘው ይኹንታ “ጉባኤ አርድእት” በሚል ራሱን ሠይሞ፣ አደራጅቶና ተልእኮ ሰጥቶ በኅቡእ ሲንቀሳቀስ የቆየው ቡድን ፀረ - ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ፀረ - ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ፀረ - መንፈሳውያን ማኅበራት በአጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት መጠናከር ይልቅ ለአባ ጳውሎስ ዐምባገነናዊ ሥልጣን መጠናከር፣ የቡድኑ አባላት በቤተ ክህነቱ በያዙት ሓላፊነት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚያሳድዱትን የግልና የጋራ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የያዘው ዓላማ ከተጋለጠ በኋላ መሥራች አባሎቼ ናቸው ያላቸው ግለሰቦች ራሳቸውን ማሸሻቸው እየተገለጸ ነው፡፡ ከእኒህም የሚበዙት ፕሮቴስንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ፣ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ላይ የሚሠራው ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ቡድኑ በኅቡእ የሚያካሂዳቸውን ስብሰባዎች በማስተባበር የሚታወቀው ብርሃኔ ገብረ ጻድቃን (በመቐለ ስሙ ብርሃነ ውሪጥ) በፓትርያርኩ ስም እያስፈራሩ ያሰባሰቧቸው የመምሪያ ሓላፊዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ይህም ኹኔታ ቡድኑ ራሱን በይፋ ገልጦ ማንነቱን የሚያስረዳ ነው የተባለ ሰነድ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት በመላክ የ‹ዕወቀኝ› ዐይነት ትእዛዝ አይሉት ጥያቄ ለማቅረብ እንዳስገደደው ነው የተነገረው፡፡ ውሎ አድሮ በይፋ መውጣቱ ግድ ቢኾንም ለፀሐይ ብርሃን መጋለጡ ያጠወለገው ወይ ያጸድቀው ይኾን የሚለውን ወደፊት አብረን እናየዋለን፡፡

በተያያዘ ዜና ራሱን “ጉባኤ አርድእት” በሚል የሚጠራው ቡድን በምን ምክንያት እንደተቋቋመና ለምንስ በኅቡእ ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ጥያቄ ያጫረባቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሐላፊዎች ለቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነት ሲባል እንቅስቃሴውን በትኩረት እየተከታተሉ መኾናቸውን ትላንት ለኅትመት የዋለው ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው በ19 ዓመት ቁጥር 20 እትሙ ያነጋገራቸው የመምሪያ ሓላፊዎች÷ “ጉባኤ አርድእት” በሚል ራሱን የሚጠራው ቡድን ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ሥራ ሊሠራ ከኾነ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ማግኘት ይገባዋል፤ ነገር ግን ይህን በመተላለፍ ለተለየ ዓላማ መሰባሰቡ አደጋ ስለሚኖረው እንቅስቃሴውን በጥብቅ እየተከታተሉት መኾናቸውን ሓላፊዎቹ መግለጻቸውን አስረድቷል፡፡

“ጉባኤ አርድእት” የተሰኘውን ቡድን ቤተ ክርስቲያን እንደማታውቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊንና የጠቅላይ ቤተ ከህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ጠቅሶ የዘገበው ጋዜጣው÷ አብዛኞቹ የቡድኑ አስተባባሪዎች በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት እያጡ የመጡ ግለሰቦች በመኾናቸው ቅዱስ ሲኖዶስ እኒህ ግለሰቦች ለመፍጠር ካሰቡት አደጋ ቤተ ክርስቲያንን እንዲታደግ ጥሪ ማስተላለፋቸውን አስታውቋል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን።

1 comment:

መላኩ said...
ፈረንጅ 666ን ሳይለጥፍ ዶክትሬቱን ሰጥቶ እንዲሁ በቀላሉ የሚያሰናብትን ይመስለናል? ያሳዝናሉና አጥብቀን እንፀልይላቸው!

Friday, 6 July 2012

ሰኔ 15 ቀን 2004 ዓ.ም  እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ::
በዘሚካኤል አራንሺ


በዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ ዘመን የነበረው ፈርኦንና የመጥምቁ ዮሐንስን አንገት ለዘፋኝ ወሮታ የሰጠው ሄሮድስ የሚያመሳስላቸው አንድ 
ዓይነት ተግባር ፈጽመዋል:: ይኽውም ሁለቱም ልደታቸውን ያከብሩ እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ መጠቀሱ ነው:: /ዘፍ.40፥20 ፤ 
ማቴ.14፥6/:: ታሪካቸውን ስናጠና ደግሞ በርካታ መመሳሰል እንደነበራቸው እንገነዘባለን:: ሁለቱም ነገሥታት ናቸው:: ሁለቱም 
ንጹሐንን አስረዋል:: ሁለቱም ደም አፍሳሾች ነበሩ:: በልደት በዓላቸውም ነፍስ አጥፍተዋል:: በልደት በዓላቸው ነፍስ ያጠፉ 
ሰዎች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ መጻፉ የልደት በዓል ማክበርን ስህተት አያደርገውም:: በጌታችን ልደት መቶ አርባ አራት ሺህ 
ሕጻናት በሄሮድስ ትእዛዝ ተገድለዋል:: የጌታችንን ልደት ግን እናከብራለን:: መግደል ኃጢአት መሆኑን እንመሰክርበት ካልሆነ በቀር 
ነፍስ በማጥፋት የሚከበር በዓል የለንም:: የፋሲካን በዓል በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለማክበር እንገደዳለን እንጂ ዘፋኞች ድግስ 
ስለሚያዘጋጁበት ማክበሩ ቢቀር ቢባል ሞኝነት ነው:: ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት በዓል ስታከብር የራሷ 
ሥርዓትና ባሕል የበዓላት መቁጠሪያ /ሊተርጂካል ካላንደር/ አላት:: የቱ መቼ መከበር እንዳለበትም ምክንያታዊ በሆነ መንገድ 
ታስረዳለች:: ጥንታዊት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆንዋም በርግጥኝነት ዕለታቱን ቆጥራ ትናገራለች:: በነቢይ የአዋጅ ነጋሪ 
ቃል ተብሎ የተነገረለት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን የልደት በዓል የምታከብረው በሰኔ ሠላሳ ቀን ነው::

የጻድቃን ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ እንደሆነ፤ ቅዱሳኑን ያገኘንባት ልደታቸውም የከበረች ናት:: /መዝ.116፥15/:: 
የመጥምቁ ዮሐንስን ልደት ያበሰረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል::” እንዳለ በልደተ ቅዱሳን ደስ 
እንሰኛለን:: /ሉቃ.1፥14/:: በዓለ ቅዱሳን የደስታ በዓላት ናቸውና:: የተወለዱበት ፥ ልዩ ልዩ ገቢረ ተዓምራት ወመንክራት 
የፈጸሙባቸው፥ ሰማእተ ኢየሱስ ሆነው መከራ የተቀበሉባቸው፥ያረፉበትና የተሰወሩበት፥ ቃል ኪዳን የተቀበሉባቸውን ዕለታት 
የምናከብረው በደስታ ነው:: ቅዱስ ዳዊት “ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና በዓል የሚያደርጉ ሰዎች 
የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።” እንዲል:: /መዝ.42፥4/:: ዕለታቱ በደንጊያ ተወግረው፥ በመጋዝ ተተርትረው ፥ ወደ እሳት 
ተጥለው፥ ለአናብስት ተሰጥተው፥ በሰማእትነት ያረፉባቸው እንኳ ቢሆኑ የደስታ በዓላት ናቸው:: የምስክርነታቸውን እውነትነት፥ 
የእምነታቸውን ጽናት፥ ታዛዥነታቸውንና ለአምላካቸው ያላቸውን ፍቅር በመግለጣቸው፤ የሚያገኙትን ክብር፥ የሚወርሱትን 
መንግስት እናስባለንና:: የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅን የከበረች የእረፍቱን ቀን በማኅሌት ከበሮ መትተን፥ጸናጽል ጸንጽለን፥ ወረብ 
ወርበን፥ ቅዳሴ ቀድሰን፥ መዝሙር ዘምረን፥ መልክ ደግመን፥ ገድል አንብበን፥ ተዓምሩን ተናግረን፥ ቅድስናውን መስክረን 
እንደምናከብረው በዓለ ልደቱንም እንዲሁ እናከብራለን:: ጠቢቡ “ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል...” ብሏልና:: 


በመወለዳቸው ደስ ተሰኝተን በዓል እናደርጋለን:: /ምሳ.29፥2/::ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ የብዙዎችን ደስታ ወልደዋል:: 
ጌታችን በወንጌል “መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ . . . ” /ማቴ.7፥17-19/:: በማለት እንዳስተማረን የመጥምቁ 
ወላጆች “በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ” ተብሎየተመሰከረላቸው መልካም ዛፎች ነበሩና:: መልካም ፍሬ ቅዱስ ዮሐንስን 
አስገኙልን:: /ሉቃ.1፥6/:: ቅድስናቸው ከፍሬያቸው ከዮሐንስ የተነሳ ገኖ ዛሬም ድረስ ይታያል:: ለብዙዎች የሚሆን ደስታን 
ወልደዋልና ስሙን ዮሐንስ አሉት ትርጓሜው ደስታ ማለት ነው:: የክርስቲያናዊ ጋብቻ ዓላማ ምእመናንን መልካም ዛፍ አድርጎ 
መትከል ነው:: ሲንከባከቡትም እንደ ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ደስታው ከቤተ ዘመድ ያለፈ መልካም ፍሬ ያፈራል:: 
በመጥምቁ ዮሐንስ ልደት “እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል . . . ” በማለት ነቢያተ እግዚአብሔር 
የተናገሩትን የትንቢት ቃል ለሚጠባበቁ ሁሉ ደስታ ነበረ:: /ሚል.3፥1 ፤ኢሳ.40፥3 ፤ማር.1፥1-5/:: የዮሐንስ መምጣት 
ለጌታችን መምጣት የምሥራች ነውና:: “ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።” የሚለው ስብከቱም የሚያስታውሰን ይህንኑ ነው:: /
ማር.1፥7/:: በዮሐንስ መጥምቅ ልደት ደስ የሚሰኘው ያለፈውም የሚመጣውም ትውልድ ነው::

በዘመኑ የነበሩትን በትምህርቱ ደስ አስኝቷቸዋል:: ትምህርቱና ተግሣጹን የሰሙትን ከስህተት መልሷቸዋልና ደስ ተሰኝተውበታል:: 
በኃጢአት ያደፈ ስውነታቸውን በንስሀ ጥምቀት አዘጋጅቷልና ደስ ተሰኝተውበታል:: አገልግሎቱን በሚገባ የተረዳ መናኒ ነበርና 
ሕይወቱ ደስ የሚያሰኝ ነበረ:: አገልግሎቱን የምታውቅ፥ ክብሩን የምትመሰክር፥ በቃል ኪዳኑ የምትታመን ቤተ ክርስቲያንም ደስ 
ትስኝበታለች:: ስለዚህም በልደቱም በእረፍቱም ቀን የደስታ በዓል ታደርጋለች:: ምእመናንም በቃል ኪዳኑ በመታመን የምናደርገው 
የመታሰቢያ በዓሉ ደስታን የሚሰጥ ነው:: በመወለዱ ያገኘናቸውን የመጥምቁን በረከቶች እያሰብን አምላኩን እናመሰግናለን:: ልደተ 
ቅዱሳንን የማዘከር ዓላማው የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ አስቦ ለማመስገን ነው:: ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት ስንናገር ወላጆቹንና 
ጽድቃቸውን የአባቱን የክህነት አገልግሎት፥ የመልአኩን ተራዳኢነት፥ የእናቱን በመንፈስ ቅዱስ መቃኘት፥ የእርሱን በማኅጸን 
መዝለል፥ የአባቱን አንደበት መክፈቱን፥ ስለ አደገበት የናዝራውያን ሥርዓት፥ ስለ አሳደገችው የበረሀ ፍየል /ቶራ/፥ ይመገበው 
ስለነበረው አንበጣና የበረሀ ማር፥ ዞሮ ያስተማራቸው ትምህርቶች፥ ስለ ፈጸማቸው የጽድቅ ሥራዎች፥ ጌታችንን ስለ ማጥመቁ፥ ስለ 
ተግሣጹና በሰማእትነት ስለ ማረፉ፥ ስለ ተዓምራቱ ከዚያም በኋላ በጸሎቱና በአማላጅነቱ ለሰው ልጆች ስለ ረዳው ርዳታ . . . 
በደስታ በማውሳት ነው:: የሌሎችም ቅዱሳንን በዓል የምናከብረው በዚህ መንገድ ነው::

እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው:: ቅድስት ኤልሳቤጥን የጎበኛት ድንቅ ነው፤ የአገልጋዩን ድካም ያልዘነጋ ድንቅ ነው፤ ዘመን 
ካለፋቸው በኋላ በእርግና ዘመናቸው ዘር የሰጠ ድንቅ ነው እያልን ደስ ተሰኝተን የምናመሰግነው በቅዱሳኑ ላይ ድንቅን ያደረገውን 
እግዚአብሔርን ነው::/መዝ.68፥35/ “ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር 
እርሱ ይዘምር።” ተብሏልና:: /ያዕ.5፥13/:: ልደተ ቅዱሳን የደስታ የዝማሬ በዓላት ናቸው:: የእግዚአብሔር ወዳጆች ቅዱሳን 
ጽናታቸው ይደነቅበታል፥ አምላካቸው ይመሰገንበታል፥ ትምህርታቸው ይነገርበታል:: ስለ ቅዱሳን በመናገር የሚጠፋ ጊዜ የለም ፤ 
ስለ ቅዱሳን መመስከርን አብነት የምናደርገው መጽሐፍ ቅዱስን ነው:: መጽሐፍ ቅዱስን እናውቃለን ለሚሉን በውስጡ የበርካታ 
ቅዱሳንን ልደት፥ እድገት፥ አገልግሎት፥ ትምህርት፥ ክብርና ጸጋ የሚመሰክር መጽሐፍ መሆኑን እንመሰክርላቸዋለን::

የመጥምቁ ዮሐንስ ልደት በዜማ በግጥም በንባብም ቢሆን የምናወሳው መጽሐፍ የመሰከረለትን እውነት ነው:: መጥምቁ ዮሐንስ 
በመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት በትንቢት ቃል “የአዋጅ ነጋሪው ቃል” ፤“የቃል ኪዳን መልእክተኛ”፤ “መንገድ ጠራጊ”፤ “በበረሃ የሚጮኽ 
ሰው ድምጽ” ወዘተ እያሉ አመስግነውታል:: መልአከ እግዚአብሔር ቅድስናውንና ክብሩን ሲናገር “ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ 
ቅዱስ ይሞላበታል፤” ፥“ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።” ብሎለታል ፤ ካህኑ ዘካርያስም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ “አንተ 
ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፤” እያለ አገልግሎቱን ገልጧል ፤ ጌታችንም “እርሱ 
የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ፥” ፤ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ 
አልተነሣም፤” ብሎ ሰማያዊ ክብሩን ገልጾለታል:: /ማቴ.11:11፤ ዮሐ.5፥35/:: ይገስጸው የነበረው ሄሮድስ እንኳን ሳይቀር 
“ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤” ተብሎ 
ተጽፏል:: /ማር.6፥20/:: የቅዱሳንን ሕይወት ማውሳት መጽሐፋዊ ነው፤ የምንለው በዚህ መንገድ ክብራቸውን፥ 
አገልግሎታቸውን፥ ቅድስናቸውን የምንመሰክር በመሆኑ ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ ኤልያስን ይመስል የነበረ ነቢይ ነው:: ዮሐንስ መጥምቅና ነቢዩ ኤልያስ አኗኗራቸው ለመናንያን አርአያ ምሳሌ የሚሆን 
ነበር:: ኤልያስ በበረሀ ኖሯል፥ ዮሐንስም እንደዚያው:: መምህራን ሲጠሯቸው መምህር ወመገስጽ ይሏቸዋል ኤልያስ አክአብን 
ኤልዛቤልን ገስጿል፥ ዮሐንስም ሄሮድስን ገስጿል:: የጽድቅ ምስክሮች ነበሩ ኤልያስ ስለ ናቡቴ፥ ዮሐንስ ስለ ሕገ እግዚአብሔር 
ተሟግተዋል:: ሌሎችም በርካታ ተመሳስሎ አላቸው፡፡ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን የልደቱን ዜና የተናገረው መልአክ 
“በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።” በማለት መሰከረለት:: /ሉቃ.1፥17/:: በነቢዩ ኤልያስ በቅዱስ ዮሐንስ መንገድ ሂደው 
ያገለገሉ መናንያንን ሰማእታትን ስውራንን ቅዱሳንን ሁሉ እነርሱን እንዳከበርን እናከብራቸዋለን:: ገድላቸውን ጽፈን ተዓምራቸውን 
ተናግረን ምስክርነታቸውን አጽንተን እንይዛለን:: የሕይወታቸውን የቃላቸውን የጽሑፋቸውን ትምህርት እንመሰክራለን:: ሕዝብ 
ደስ እንዲለው:: ለሕገ እግዚአብሔር የሚቀኑ ስለ ደሀ መበደል ስለ ፍርድ መጓደል የሚታገሉ ጻድቃን ይበዙ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ 
በዮሐንስም መንገድ የሚመጡ ጻድቃን ለማፍራት ይረዳልና::/ምሳ.29፥2/::

የቅዱሳንን በዓል ማክበር የሚጠቅመው በረከታቸውን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን የቅዱሳኑን ትምህርት ለመያዝም ነው:: በዓለ ቅዱሳን 
ሲከበር ትምህርታቸውም ይዘከራል:: የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ትምህርቶች በአራቱም ወንጌላውያን ተዳሰዋል:: የመጥምቁ ታላላቅ 
ትምህርቶች በሁለት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ:: የመጀመሪያ ትምህርቱ የንስሐ ጥሪ ነው:: ሕዝቡ እንዲመለሱ ይሰብካል ፥ 
ደንዳና ልብ የነበራቸውን እንደ ሄሮድስና የአይሁድ መምህራን ያሉትን ይገስጻል:: ይህ ትምህርቱ ዘመኑን እየዋጀ በየዘመናቱ የሚነሱ 
ምእመናንን ሕይወት ለማነጽ ይጠቅማል:: ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ለመጡ ለሕዝቡ ቸርነትን ስለ ማድረግ፥ ለቀራጮች ስለ እውነት 
ሚዛን፥ ለጭፍሮች ስለ ፍትሕ፥ . . . ያስተማራቸው ትምህርቶች ዘመናትን እየተሻገሩ የሚመክሩ ሁለት አፍ ያለው ሰይፍ ናቸው::/
ሉቃ.3፥11-14/:: የንስሐ ትምህርት ተግሣጽና ምክር ይሰጣል:: ከመጥምቀ መለኮት ከቅዱስ ዮሐንስ ትምህርት የተወሰደ ነው:: 
በዚህምክንያት ነው በዓለ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠናባቸው፥ የሚነገርባቸው፥ የሚተረጎምባቸው 
ናቸው የምንለው::


ሁለተኛ ነገረ ሥጋዌ ላይ ያተኮረው ትምህርቱ ነው:: መጥምቁ ዮሐንስ የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢርን ሲያስረዳ መሲህ ይመጣል 
ተብሎ በነቢያት የተነገረው በጌታችን መፈጸሙን አስረግጦ የተናገረ መምህር ነው::/ዮሐ.1፥29-36/:: የዓለም መድኃኒት መሆኑንም 
ከመልአኩ ቀጥሎ የመሰከረ ነቢይ ነው:: “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ብሎታልና:: በሥጋ ልደት 
ቢቀድመውም ለመለኮት ዘመን አይቆጠርለትምና ቅድመ ዓለም የነበረ ሕልውናውን “ከእኔም በፊት ነበር” ሲልም መስክሯል:: 
የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅን ምስክርነት ልዩ የሚያደርገው ነገርም አለ:: ምስክርነቱ የእውቀት ብቻ አይደለም:: በዮርዳኖስ ባሕር ቆሞ 
ጌታውን ሲያጠምቅ ሰማይ ተከፍቶ ያየ የእግዚአብሔር አብን ምስክርነት የሰማ የምስጢር ሰው ነው:: አይሁድን ያሳፈረበት ትልቁ 
ምስክርነቱም “እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ።” የሚለው ነው:: የነገረ ሥጋዌ ትምህርቱን 
ሲደመድም “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ 
ሕይወትን አያይም።” ሲል የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን በሚገባ አስረድቷል:: /ዮሐ.3፥25-36/:: ጌታችንም የምስክርነቱን 
እውነትነት “እናንተ ወደ ዮሐንስ ልካችኋል እርሱም ለእውነት መስክሮአል።” በማለት ገልጿል:: /ዮሐ.5፥33/:: በዓለ ቅዱሳን 
በጠቅላላ ነገረ እግዚአብሔር የሚነገርባቸው፥ ትምህርተ ሃይማኖት የምናጠናባቸው፥ ታሪከ ቤተ ክርስቲያን የሚዘከርባቸው በዓላት 
ናቸው::

በአጠቃላይ በዓለ ቅዱሳንን አታክብሩ ማለትን የሚያህል የወንጌል እንቅፋትነት የለም:: ጌታችን ባለሽቱዋ ማርያም በንስሐ እንባ 
አጥባ ሽቱ ቀብታ መልካም አድርጋለችና ለውለታዋ መታሰቢያ ሲያቆም “እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ 
በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።” ካለ:: /ማቴ.26፥13/:: ስለ 
ስሙ እስከ ሞት ድረስ ለተደበደቡ፥መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ፥ በእስራትና በወኅኒ ለተፈትኑ፥ በደንጊያ ተወግረው ለሞቱ፥ በመጋዝ 
ለተሰነጠቁ፥ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ለተቅበዘበዙ . . . ወዳጆቹማ እንዴት ያለ 
መታሰቢያን ይሰጣቸው? የወንጌል ትምህርት ለሚተረጎምባቸው አብነቶችማ እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም?

በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ቅዱሳን ሥርዓታዊና ትውፊታዊ በሆኑ መንገዶችም ይዘከራሉ:: ሥርዓታዊው መንገድ ገድልና 
ተዓምር መጻፍ፥ ድርሳንና መልክ መድረስ፥ በስማቸው መቅደስ መሰየም፥ . . . ናቸው:: ትውፊታዊውም “ማንም ከእነዚህ 
ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።” ከሚለው 
አማናዊ ቃል ኪዳን ለመሳተፍ በቅዱሳኑ ስም ጸበል ጸዲቅ ማድረግን የመሰሉ ናቸው:: በመጥምቁ ዮሐንስ ስም የሚሰበሰቡ 
ወዳጆቹም ገድሉን አንብበው፥ ተዓምሩን ተናግረው፥ ለነዳያን መጽውተው፥ ሰማእቱን ያዘክራሉ:: በልደቱ የወላጆቹን ሐዘን ያራቀ 
በምልጃው ለሚተማመኑ መታሰቢያውን ለሚያደርጉ ወዳጆቹም ደዌያቸውን እያራቀ መንፈሳዊ ደስታን ያለብሳቸዋል::

የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ የልደቱ ረድኤትና በረከት አይለየን:

Thursday, 5 July 2012


ቤተ ክርስቲያን “ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ” በሚለው ወይም በ“ያ ትውልድ” ቁጥጥር ሥር፦ የዳላስ ተሞክሮ


(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 20/2010)፦ ይህ ጽሑፍ በቅርቡ በተከታታይ ስናስነብባችሁ እና በዩ-ቲዩብም ስናሳያችሁ የቆየነው “የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ተከታታይ” ሳይሆን ከዳላሱ ጉዳይ በመነሣት የቀረበ አጠቃላይ ምልከታ ነው። ርዕሱን የበለጠ ለመረዳት ግን ሁለት መሠረታዊ አባባሎችን መገንዘብ ያስፈልጋል። እነዚህም “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” እና “ያ ትውልድ” የሚሉት ሐረጎች ናቸው። እነዚህ ሁለት ወካይ ሐረጎች አሁን ኢትዮጵያን በመምራት ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ እና የኢህአፓ መታወቂያዎች ናቸው። ኢሕአዴግ ስለ ራሱ ገድል ያወጣቸው የነበሩት (የነተስፋዬ ገብረ አብ) መጻሕፍት የሚታወቁት “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” በሚል ሲሆን ስለ ኢሕአፓ ታሪክ በሰፊው ያተተው የፓርቲው መሥራች ክፍሉ ታደሰ የጻፋቸው መጻሕፍት ደግሞ “ያ ትውልድ” ይባላሉ። ይህ ጽሑፍ እነዚህ ሁለት ትውልዶች ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጃቸውን እስካላነሱ ድረስ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነጻነት እንደሌላት ለማጠየቅ ይሞክራል።

ቤተ ክርስቲያን እኛ ልጆቿን ከኃጢአት ባርነት ነጻ ያወጣች፣ በእናትነቷ ደግሞ እኛን የወለደች እና በሰማያዊ ጸጋ ያሳደገች፣ በአገርነቷ ያሉንን መንፈሳዊና ዓለማዊ ቅርሶች የለገሰች ናት። ይሁን እንጂ ይህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን እርሷ ነጻ ባወጣቻቸው ልጇቿ የባርነት ቀንበር ሥር የምትገኝ “ገባር” ናት። በአገር ቤት በኢሕአዴግ ቁጥጥር ሥር፣ በውጪው ዓለም ደግሞ በአብዛኛው በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ሥር የምትገኝ፤ በዚህም ሆነ በዚያ የራሷ ድምጽና አንደበት የሌላት ቤተ ክርስቲያን ናት። በተለይም ኮሚኒስታዊው የአብዮት ማዕበል በአገራችን ከነፈሰበት ከ1966 ዓ.ም (1974) ወዲህ ወታደራዊው የመንግሥቱ ኃ/ማርያም አገዛዝም ሆነ ሌላኛው ኮሚኒስታዊው የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ከቤተ ክርስቲያን ጫንቃ ላይ አልወረዱም። በውጪው ዓለም ደግሞ ከኮ/ል መንግሥቱ ጋር የነበሩ፣ ወይም በአጼው ዘመን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ይገኙ ነበሩ እና ዘር ቆጣሪ ዘመዶቻቸው፣ ወይም ኢሕአፓ እና ኢሕአፓን መሰል ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ቤተ ክርስቲያንን ተቆጣጥረዋል። እንግዲህ “እናንት ልጆቿ እባካችሁ ለእናታችሁ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነጻነቷን መልሱላት፣ ከቀንበራችሁ አሳርፏት፣ የከበደ መዳፋችሁን አንሱላት” ስንል ሁሉንም ወገን ማለትም በአገር ውስጥ ያለውንም በውጪው ዓለም ያለውን የዳላስ ሚካኤሉንም ዓይነት አገዛዝ ማለታችን ነው።

በአገር ውስጥ
በአገር ውስጥ ያለው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በኢሕአዴግ ፓርቲ ቁጥጥር ስር የወደቀ አስተዳደር ነው። ከቅ/ሲኖዶሱ ድምጽ ይልቅ የፓርቲው ድምጽ የበለጠ ተሰሚነት አለው። ሌላው ቀርቶ በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ላይ አባቶች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው መመሪያ እስከመስጠት የሚደፍር “ደፋር” ፓርቲ ያለበት አገር ነው። ቤተ ክህነቱም የመንግሥትን ድምጽ እየተከተለ “አብ ሲነካ ወልድ ይነካ” እያለ “መንግሥትን የሚነካብኝን ሥጋውን ለመከራ ነፍሱን ለሰይጣን” እስከማለት እንዲደርስ ያደረገ ፓርቲ ነው። በየትኛውም የቤተ ክህነቱ እንቅስቃሴ ውስጥ የመንግሥት ሚጢጢ ካህን-መሰል ካድሬዎች ተሰግስገውበታል። እውነቱን ለመናገር ኢህአዴግ ቤተ ክህነቱን የሚንቀውን ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱን ደግሞ በእጅጉ ይፈራታል። ጥርስ እንደሌለው አንበሳ የሚመለከታትን ያህል እንዳሸለበ አንበሳም ይፈራታል። አንድ ቀን ብትነሣ ጉዴን ታፈላዋለች ብሎ ይሰጋል። ስለዚህም በዘር ላይ በተመረኮዘው ወገንተኝነቱ “ዘመኑ የነ እንትና ነው” የሚሉ ደቀ መዛሙርቱን በማሰለፍ በአባቶችና በአገልጋዮች መካከል ወደፊትም ሊያመረቅዝ የሚችል ጠባሳ በመጣል ላይ ይገኛል።

በውጪ አገር
በውጪው ዓለም ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በአብዛኛው በተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጠለፈ ነው ማለት ይቻላል። በኢትዮጵያ ኢህአዴግ የሚውልባትን ግፍ፣ በውጪው ዓለም ደግሞ ሌሎቹ ፓርቲዎች እየደገሙት ነው።  አብዛኞቹ ካህናት የእነርሱን ፖለቲካ እንዲደግፉ፣ ባይደግፉም አፋቸውን ይዘው ቁጭ እንዲሉ ያስገድዳሉ። በዐውደ ምሕረቱ የፖለቲካ ማስታወቂያቸውን ይናገራሉ፣ ውግዘታቸውን ያስተላልፋሉ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ይጥሳሉ። ለእነርሱ የማይገዙ ካህናትን አዋርደው ያባርራሉ። የሚቃወማቸውን በሙሉ “በወያኔነት” ፈርጀው ስሙን ያጠፋሉ። ከዚህም አለፍ ሲል ደግሞ ለራሳቸው እንዲመቻቸው ባደረጉት እና “ስደተኛ ሲኖዶስ” ባሉት ተቋም አማካይነት ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት የማይታዘዙትን፣ ከአገር ቤት በተለያየ የሃይማኖት ችግር የኮበለሉትን፣ ሥነ ምግባርና ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የሌላቸውን በጉያቸው አቅፈው ይኖራሉ።

በውጪ ያለው የቤተ ክርስቲያን ስብጥር ገለልተኛ፣ ስደተኛ እና የአባ ጳውሎስ  በሚል ኢ-ክርስቲያናዊ አከፋፈል የተቧደነ ሲሆን የቤተ ክርስቲያናችን ለዛና ወዝ ምጥጥ ብሎ ጠፍቶ ሃይማኖተኛው በፖለቲከኛው እግር ስር ወድቆ የሚገኝበት ሁኔታ ሊፈጠር በቅቷል። በዚህም ምክንያት ሥርዓት-አልበኝነት በመንገሱ ክህነት የሌላቸው “ክህናት”፣ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ቦርዶች፣ የኑፋቄ ትምህርት የሚያስተምሩ ሐሰተኞች ተቀላቅለው ሃይ የሚባልበት ቦታ ጠፍቶ ሁሉም ተተረማምሷል። አንድ ሰው በሚያጠፋው ጥፋት ተጠያቂ የማይሆንባት ባለቤት አልባ ቤተ ክርስቲያን እየተፈጠረች ነው። በዳላስ ሚካኤል እየሆነ እንዳለውና በሌሎችም ቦታዎች እንደሆነው ባለቤት ስለሌላት ጉዳያችን በሙሉ ወደ ፍርድ ቤት እየሄደ መሳቂያ እና መሳለቂያ ሆነናል። የፖለቲካና የግል ጥቅም ዓላማ እንጂ ሌላ ግብ የሌላቸው፣ በቅጡ ከሲጋራ ሱሳቸው እንኳን ያልተላቀቁ፣ በሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ጸሎት የማይሳተፉ፣ እምነቷን የማያከብሩ ነገር ግን አስተዳደሯን የተቆጣጠሩ “ቦርዶች” ታላቂቱን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወደ ገደል እየመሯት ነው።


ምን ይሻላል?
የዚህ ችግር መኖር ገና ዛሬ ለእኛ የተገለጠ አዲስ “መገለጥ” አይደለም። ችግሩ የገባቸው ብዙዎች ናቸው። ይሁን እንጂ ገና አንገታቸውን ቀና ሲያደርጉ “ወያኔዎች ናቸው፣ ቅንጅቶች ናቸው፣ ቤተ ክርስቲያናችንን ለአባ ጳውሎስ (ለአባ መርቆርዮስ) ሊሰጡብን ነው፣ ጎበዝ ተነሥ፣ ማህበረ ቅዱሳን ናቸው፣ አድሃሪዎች ናቸው” እያሉ አንድም ሃይማኖታዊ ነጥብ በሌለው ክስ ስሙን ያጠፉታል።

መፍትሔው አጭር ነው። የቤተ ክርስቲያንን ለቤተ ክርስቲያን፣ የፖለቲካን ለፖለቲካ። በየቡድኑ ተቆርቁዳችሁ የተቀመጣችሁ እና የቤተ ክርስቲያናችሁ ጉዳይ የሚያስጨንቃችሁ አበው ካህናት፣ ምእመናን ቤተ ክርስቲያቱን ከዚህ ዓይነቱ አሳፋሪ ሸክም ልንገላግላት ይገባናል። ለዕለት ጉርስ ብላችሁ አፋችሁን የከደናችሁ፣ ዓይናችሁን የሸፈናችሁ ብትኖሩም ቢያንሰ በጸሎት ልትረዱ ይገባል። ለጊዜያዊ ጥቅም ብላችሁ የቦርድ ወይም የመንግሥት ሰባክያን የሆናችሁ ሰባክያነ-ቦርድም/ ሰባክያነ-ፖለቲካ ከታሪክ ተወቃሽነት ራሳችሁን ማዳን ይገባችኋል። በአገር ቤት ያለው የመንግሥት ከባድ እጅ ከቤተ ክርስቲያናችን ላይ እንዲመነሳ አጥብቀን የምንጮኸውን ያህል በውጪ አገርም ያለው እንዲስተካከል መጮኽ ይኖርብናል። እባካችሁ ለቤተ ክርስቲያን ነጻነቷን መልሱላት!!!


ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

27 comments:

Anonymous said...
sometimes, I thought something like this- we have take forceful action. we have to punish those who are playing a game on the church whether papas or mi'emen.
One day a courageous man shold do this.
Anonymous said...
i support your idea for the first time. this is independant mind. I love it and i will support it.
selamawi said...
በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን


ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፥10

መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።

ወደ ቲቶ 3 10፥11

ይህንም እላለሁ። እያንዳንዳችሁ። እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፥12

ከላይ የቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል ለማስታወስ እንደሞከርኩት ቤተክርስቲያናችን የምትሰብከው እውነተኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል እኛ ማን እንደሰበከንም ማወቅ የተሳነን ይመስለኛል እባካችሁ ሰዎችን አንመልከት በቃሉ ብቻ እንመራ ሰዎች በሚዘረጉት መንገድ አንጓዝ እግዚአብሔርን ብቻ እንከተል እውነቱ የት እንዳለ እያወቅን ለስጋዊ ጥቅምና ለዘረኝነት ቦታ አንስጥ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንደሆነች ምንጊዜም ንጽህት ናት ብናጠፋ ብንበድል እራሳችን እንጠፋለን እንጅ ቤተክርስቲያንን አንጎዳትም ስለዚህ ለሰላምና ለይቅርታ ልባችንን እንክፈት የሰላም አምላክ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታዉን እና ምህረቱን ያውርድልን ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመሰቀሉ ክቡር አሜን ,,,
Anonymous said...
Dear Dejeselam,
You are a living evidence for the inevitable freedom of our beloved church from the tribal thugs, the day time robbers, the taxi driving and parking lot bandits, the ehapa derg & woyane murderers who have been hell bent all along to disrupt, weaken and control the church so that they can spearhead their futile political agenda which usually is designed to oppress the peace loving people and pillage the country Ethiopia. I was hoping that one day Mahiber Kidusan to liberate the church from the stranglehold of the poisonous and parasite Ethiopians, unfortunately it seems that the Mahiber is spineless, dangerous, wicked, and righteous all at once just like the Lucifer. Therefore, the key lies in the hands of independent minded Ethiopians, which i thing the editor/s of this blog sphere rightly represents. Please, use it wisely.
Anonymous said...
ደጀ ሰላምን

ገና ዛሬ ቁም ነገርና ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን የወገነ ሀሳብ ስታቀርብ አገኘኋት ::

የእኛ ችግራችን እኮ : ችግሩን በግልጽ እያወቅነው :
በቀጥታ ችግሩን ከመግለጽ ይልቅ : የራስን የቡድን ስሜት በሌላው ክፍል ላይ ለመጫን የሚደረገ ጨለምተኛነት ነው ::

እኔ ከምስማማባቸው ነጥቦች መካከል

1. በውስጥም በውጭም ያለችው ቤተ ክርስቲያናችን በፖለቲካኞች ስር መውደቋ

2. ይህን ክፍተት ተጠቅመው በውስጧ የተሰገሰጉት መናፍቃን እና ፀረ ቤተ ክርስቲያን/ሃይማኖት የሆነው አጥፊ ተግባራቸው ::

3. ዓላማ የሌላቸው እና ለጥቅማቸው ብቻ ያደሩ : ከዛም በላይ በአንድ እጃቸው መስቀል በሌላው እጃቸው የፖለቲካ መሳሪያ ያሆኑ : ካሕናት መበራከት ::

ሲሆኑ :

[u]ለዚህ ሁሉ ችግራችን መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስበው[/u]

በመጀመሪያ ደረጃ : በሁለቱ አባቶች (አቡነ መርቆሬዎስና ዐቡነ ጳውሎስ) እና በተከታዮቻቸው መካከል ያለው ቅራኔ የሚፈታበትን ሂደት ለማሳካት መረባረብ ::

ቤተ ክርስቲያኗ አንድ አስተዳደር መከተል ከጀመረች : ኃይሏን አሰባስባ :
. ከመንግስት ጣልቃ ገብንተ ራሷን ለመከላከልና
. በስጧ የተሰግሰጉ መናፍቅቃንን ነቅሶ ለማውጣት ትችላለች ::
Anonymous said...
ደጀ ሰላምን

ገና ዛሬ ቁም ነገርና ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን የወገነ ሀሳብ ስታቀርብ አገኘኋት ::

የእኛ ችግራችን እኮ : ችግሩን በግልጽ እያወቅነው :
በቀጥታ ችግሩን ከመግለጽ ይልቅ : የራስን የቡድን ስሜት በሌላው ክፍል ላይ ለመጫን የሚደረገ ጨለምተኛነት ነው ::

እኔ ከምስማማባቸው ነጥቦች መካከል

1. በውስጥም በውጭም ያለችው ቤተ ክርስቲያናችን በፖለቲካኞች ስር መውደቋ

2. ይህን ክፍተት ተጠቅመው በውስጧ የተሰገሰጉት መናፍቃን እና ፀረ ቤተ ክርስቲያን/ሃይማኖት የሆነው አጥፊ ተግባራቸው ::

3. ዓላማ የሌላቸው እና ለጥቅማቸው ብቻ ያደሩ : ከዛም በላይ በአንድ እጃቸው መስቀል በሌላው እጃቸው የፖለቲካ መሳሪያ ያሆኑ : ካሕናት መበራከት ::

ሲሆኑ :

[u]ለዚህ ሁሉ ችግራችን መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስበው[/u]

በመጀመሪያ ደረጃ : በሁለቱ አባቶች (አቡነ መርቆሬዎስና ዐቡነ ጳውሎስ) እና በተከታዮቻቸው መካከል ያለው ቅራኔ የሚፈታበትን ሂደት ለማሳካት መረባረብ ::

ቤተ ክርስቲያኗ አንድ አስተዳደር መከተል ከጀመረች : ኃይሏን አሰባስባ :
. ከመንግስት ጣልቃ ገብንተ ራሷን ለመከላከልና
. በስጧ የተሰግሰጉ መናፍቅቃንን ነቅሶ ለማውጣት ትችላለች ::
Atnatewos said...
Atnatewos

It is fantastic and very very true article.
- The 1960s generation is passing soon.Now stand the new generation with your new and energetic power.God will be with you.
- Learn from Abune Shinoda of Egypt coptic church.They were in the same problem some 10 years back.Now their church administrative and spritual problems are solved.Their only problem is extrem muslims attack.
- Both TERARA YANKETEKETE TIWLID and YA TIWLID actors shouldn't feel bad with the fact that is written here above.Becouse it is not difficult to think as if they did all just by thinking for their mother land-Ethiopia.But past exeperiance show us all failurity.So shoudl we continue in the same way? NO BIG NO!!!!!
- Pick up your visible and invisible hands from church.You will see all what you wish to see.Since all of us are under the hands of our Almight God, we all shall get our lessons according to our acts.
YE ABATOCHACHIN AMLAK YILEMENEN
AMEN
Atnatewos
Anonymous said...
I admire the content of the article,but for some reason, it lefe me with a feeling that I am being set up to accept someone's agenda in the end?

one of the remedies for most of the problems in the Ethiopian orthodox tewahedo chruch here and in Ethiopia is the lack of unity among her followers of the faith.
We need ot bring our church fathers and resolve their differences. One hugh shortcoming of this DejeSelam is the absence of this topic in its leading article/postings. As is the case in past postings, this article does not put forth the need for the unity of church fathers. I know it is not be mistake and it bothers me.

My other comment is that, it is a known fact that Mahebere kedusan plays a big role in the shaping of the church's current conditions in Ethiopia and aboard. Most of the blame pointed at the others groups in the article can fairly be pointed at this group. The case in point is the situation at Dallas Kidus Mikael. MK needs to learn there is victory in loosing xsome battles. Bemeshenf Mashenef ...
Anonymous said...
This article assumes that Woyane and EPRP are the forces that are damaging the health of our church. It streaches a bit further and gives them credit for the "Synod in Exile" ...

I admit that politically-driven Ethiopian have heavely affect the dynamics of the chruch. However, there are those of us, who are not Woyane and are not old enough to have been in EPRP? We see what we do not like at church. We object many activities done in our chruches in the name of the church. We do not like ot see those who put their group's abjective before that of the church, including Mahebere Kidusan. We would like members of MK to take part in many church affairs, but we also want them to stop some the dominance they want ot have in many church affairs.

We are not Woyane, EPRP, or Menafikan ... Do not forget to include our concerns in the next parts of your article. I have a feeling anyone who even wants to give constructive feedback to members of the group is seen as opponent. So, surprise me by not labeling me and my kinds as Menafik and admit some of the mistakes, take responsibility and share that with us.
tewodros said...
Are u kidding me!
Stop and analyze your history once , let’s go back to the 3rd century ,we find great bishop and great kings.Abune selam and king St.Ezana & king St.Sizana , starting from them we have been using the political power for our church benefit. Even before that the Ethiopian jandereba went to Jerusalem why one of the reasons is he was government trader.
All our fathers prioritize their religion from their political stage. So They used it all. We are all very gready ,selfish, illiterate ,in love with abroad , hate each other….generally we all prioritize this world zan our spiritual life.
I sent a message for many peoples saying “ which party’s idea is good for our church?” No body cares or nobody wants to say it to me. One thing I was sure no body knew for sure. Let me tell u one thing z protestants are already competing in this election as a party . What exactly were u saying ,<< z politics should leave us alone.>> My brothers u are sleeping. wake up and start z rite politics ,otherwise the others will rotate us as they like. I hope u know where that takes church. And … I am sorry to say it but it is painful truth. There will be no Ethiopian orthodox church soon.
May God be with us all.
tewodros said...
Are u kidding me!
Stop and analyze your history once , let’s go back to the 3rd century ,we find great bishop and great kings.Abune selam and king St.Ezana & king St.Sizana , starting from them we have been using the political power for our church benefit. Even before that the Ethiopian jandereba went to Jerusalem why one of the reasons is he was government trader.
All our fathers prioritize their religion from their political stage. So They used it all. We are all very gready ,selfish, illiterate ,in love with abroad , hate each other….generally we all prioritize this world zan our spiritual life.
I sent a message for many peoples saying “ which party’s idea is good for our church?” No body cares or nobody wants to say it to me. One thing I was sure no body knew for sure. Let me tell u one thing z protestants are already competing in this election as a party . What exactly were u saying ,<< z politics should leave us alone.>> My brothers u are sleeping. wake up and start z rite politics ,otherwise the others will rotate us as they like. I hope u know where that takes church. And … I am sorry to say it but it is painful truth. There will be no Ethiopian orthodox church soon.
May God be with us all.
elganan said...
እኔ ማጋነን ካለሆነ አገር ውስጥ ያለው ምንም አላረገም እንደውም ቤተክርስቲያን ራሶን ትቻል በማለት በተደጋጋሚ የሰብካል ግን እሚሰማ ጠፋ ለምሳሌ አንድወቅት ፃፃሳሳት መለስ ዜናዊ ጋር ገብተው ያላቸውን አውቃለሁ ስሩ ህዝበን አታወናብዱ ነው ያላቸው ግን ለዚህ ልተፈጠሩም አባቶቻችን በውነት ነው የምለው ምንም እንቅፋት የለም አየቸዋለሁግታየ ለማንኛውም መልካም
Anonymous said...
እግዚኣብሔር ይባርካችሁ ደጀሰላማውያን፡
ይህን የመሰለ ያላዳላ ትክክለኛ ጽሑፍ ማቅረባችሁ ብእውነት በጣም እናመሰግናችሁ ኣለን።
እውነትና ግንባር ኣይሸሸግም እንደሚሉ ኣበው፡
ያቀረባችሁ ኣስተያየት በጣም የሚደገፍና ሁላችንም ልናስብበት የሚገባን ጉዳይ ነው።
ግን ኣንዴ ላስታውሳጭሁ።
ቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ምስጥ የሆንዋት፡ ፖለቲኮኞች ብጃ ኣይደሉም።
ኣቡነ ጳውሎስና ኣቡነ መርቆሬዎስም ለብቻቸው ኣይደሉም።
እውነቱን ማወቅና መድኃኒት ልንፈልግለት የሚገባን ጉዳይ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ነው።
ይህ ማኅበር፡ ለቤተ ክርስቲያናችን፡ በጣም ኣደገኛ ስብስብ ነው፡ በዚህ ኣደገና ድርጅት ያልተሰደበ ጳጳስ። ፓትርያርክ፡ ካህን፡ ዲያቆን፡ ወጣት ኣለ ለማለት የሚቻል ኣይመስለኝም፡ የእነሱን ሓሳብና መንገዲ ያልተቀበሉ ሁሉ፡ መናፍቅ፡ ከሓዲ፡ ኦርቶጰንጤ፡ ተሓድሶ፡ ወዘተ የሚል ጥላሸት በመቅባት ስምን በማጉደፍ፡ እንደ ተዋጊ ቀንዳም በሬ፡ ከቤተ ክርስቲያን ያባረርዋቸውና ያጠፍዋቸው ኣማንያን ስፍር ቁጥር የላቸውም።
ከመናፍቃን ጋር፡ ገዥና ሸያጭ የተስማሙ ነው የሚመስለውን፡
ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምን እንድታገኝ፡ ይህ ማኅበር ኣካሄዱን ተመልሶ መገምገምና ማረብ ኣለበት ባይ ነኝ።

በደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይጠብቅ ኣምላክ። ኣሜን
elganan said...
እኔ እምለው መኅበረቅዱሳን ያስወጣቸው እነ ማን ናቸው ? እባ ብእሴ አባ ዮናስ አባ ዘውዱ ስለዚህ እነዚህ እቤት ምቀመጥና ቤተክርስቲያንን መበጥበት ነበረባቸው? አልገባኝም ሰለማህበረ ቅዱሳን የሚነገረው ሲመስለኝ ማህበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች ችግር ያለባቸው ይመስለኛል በተረፈ በተክርስቲያንን መጫወቻ ለማረግ ከልሆነ ማህበረ ቅዱሳንን መጥላት አያስፈልግም ወይም መቃወሚያችንን በትክክ እናሰቀምጥ እና ሁላችንም እንመን
Anonymous said...
Iam always surprized when I see comments against mahibere kidusan. Every thing people relates to MK? what do u think is the reason?why do not you see its true history and fruitful activities in the church.The only reason why most educated individuals across the country engaged to love EOTC is mainly because of MK's activities in the colleges and universities.I do not want to forget a very important contribution of sunday schools and few dedicated church fathers who want to the see the participation of the youth in church activities. pls let us think strategically than uttering here and there with out objectives.with regards to the above posted topic it quite true that politics tries to suppress our church's develpment and participation of is members in orgnising the church to make forward the way to liberyand freedom from earhly deeds. By the way the true democrate in the world is only Our Lord who gave us freedom to choose and live based on our free will.
may God give us our church chance to rise up again!
Anonymous said...
ይቺን የላይኛዋን አስተያየት የሰጠህ ወንድም ያልገባህ ነገር ያለ ይመስለኛል ::እነዚ ማሀበረ ቅዱሳኖች እኔ ሳውቃቸው ካገር ቤት ጀምሮ ጥሩ ሲሰሩ እንጂ ሲሳደቡ አላየሁም:: እንደውም ብዙ ተሃድሶና መናፍቆች ሲሰድቡዋቸው ዝም ማለታቸው ያናድደኛል :: እንዳንተ አይነቶቹም የሚሳሳቱት እነሱ ስለራሳቸው ስለማይናገሩ ይመስለኛል
ለማነኛውም ስራቸውን ለማየት ስትሞክር እውነቱን ታገኛለህ::

እንዲየውም ጌታ እነሱን ባያስነሳ ኖሮ ዛሬ መናፍቅ ሀገሪቱን በተቆጣጠረ ነበር ::
እረ እንዲየዉም ያበርታቸው!
elganan said...
እኔ የሚገርመኝ ጠላት በተነሳ ቁጥር ማህበረ ቅዱሳን ላይ መዛቱ አይቀሬ ነው እስቲ የምታወቁ ከሆነ የአባልነት መመዘኛውን ንገሩንገሩን ዎንድሞቸ እኔ ሳስብ አብሬ ማገልገል ይሰማኛል ስለዚህ ካወቃችሁ እርዱን ከላይ የሰጠሁት አስተያየት ምንም መልስ አላገኘም ናነው!!!
maki said...
የኢትዩጵያ ቤተክርስቲያን ችግር ያለፀሎት ያለ ጾም የሚፈታ አይደለም ሁሉም ለራሱ ጥቅም ሲል እንጂ ለቤትክርስቲያኗ አሰቦ በጐያዋ ያለ የለም በተለይ ጳጳሳት በሁለቱም ሲኖዶስ ጋር ያሉት፡፡ ለቤተክርስቲያኗ ቢያስቡ ኖሩ ቀኝ ባልተገዛች ሀገር ሁለት ሲኖዶስ ባልኖረ ነበር፡፡ በተለይ የሁለት ሲኖዶስ ጉዳይ ችግሩ ያለው በውጪ ሀገር ነው ኢትዩጵያ ውስጥ በሁለት ሲኖዶስ ምክንያት ምንም አልተቸገርም፡፡ ጳጳሳቶቾ ግን ውስጥን በሚበላ መልኩ ፖለቲከኖች፣ ካድሬዎች ፣ ሙሰኞች እና ዘረኖች ናቸው፡፡ እኔ በግሌ ውጪ ላላችሁ ኢትዩጵያውን የምመክረው አሁን የኢትዩጵያ ሕዝብ እየተከተለ ያለውን መንገድ እንድትከተሉ ነው ማለት ከምንም ነገር በላይ ቤተክርስቲያን ትበልጣለች ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ሰውም በሰው ይተከካል እናት ቤተክርስቲያንን ግን የሚተካት የለም የሰውን ነገር ተውት ቤተክርስቲያን የማምን ፖለቲከኛ ቤት አይደለምችም ማንም ፖለቲከኛ በቤተክርስቲያን መጠቀም የለም ምክንያቱም ቤትክርስቲያን በሰው ስትያዝ መሪዋን ሰው ስናደርግ የቤተርስቲያኗ ባለቤት መንፈስ ቅዱስ ይወጣል፡፡ ስለዚህ እኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉት ሰዎች መሻል እንደውም መብለጥ አለብን ማንኛውም ሰው እኛ ካልተቀበልናቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ የፈለጉትን የማድረግ መብት የላቸውም፡፡ ተባብረን ቤተ ክርስቲያናችንን አናጥፋ፡፡

የቅዱሳን አምላክ እ/ር ለቤተክርስቲያናችን ሰው ይላክልን አሜን
Anonymous said...
I have tried to written previously to your site. I have discovered that you are biased and not allow free idea be expressed. If you continuing barring comments that has truthful and factual the negative side of Maheber Kidusan, and you are not publish it. Why it is? How do you contributed for the organization that only you post the positive side alone. There is different website that moderated the ongoing issue of the Dallas Church as http://www.tadias.com and http://www.abugidainfo.com/amharic/ and other as well. You have also the actual website of the Church http://stmichaeleoc.org/ for a better understanding of the issue than yours one side story. For me you are serving only your group than all-Ethiopians. Open up
ደጀ-ሰላም said...
To the Anonymous above,

Yes, we moderate comments to fence out unethical people who have no decency of matured dialogue. Since you are not using any name, we could not know if you have previously written us or not. Still, you blamed us to be partisan but not substantiate your comments with evidence. If you think our reports are not fair and true, then challenge us. By the way, Deje Selam will continue to write on Dallas case in depth, with the will of God. It is time to defend our Church; nothing but the Church, so help us God.
Cher Were Yaseman,
DS Team
Anonymous said...
እኔ በእውነቱ ብዙም ነገሮችን ጠለቅ ብዬ ባላውቅም አንዳንድ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት ግን ይገርማል
በመጀመሪያ ደረጃ አባቶችን ታውቋቸዋላችሁ? በተለይ በኢትዮጵያ ያሉትን:: ልካችሁን ብታውቁ ጥሩ ነው ቢያንስ እዚህ ከምንጽፈው የሚበልጥ የአገልግሎትና የቅድስና ሕይወት አላቸው ሁላችሁም ይህን አታጡትም::ነገር ግን በድፍረት ለመሳደብ ትፈጥናላችሁ ጽድቅ በስድብ አይሰራም::
ezih ethiopia yaluten abatoch yetewesenutinim bihon awkachewalehu betikikil le K/BETEKRISTIYAN agelgilot yemifatenu nachew min albat egna yemanawkachew bizu negeroch sileminoru zim bilen negerochin bandefedifibachew melkam new elalehu.
yalutin chigiroch lemekref ende meftihe yemasibew
1. ezih blog lay asteyayet yeminisetim hone yeminaneb sewoch betikikil sile k/BETEKRISTIYan andinet kelib honen entseliy yetselotachinin waga GETA aynesanim ena
2. abatochin yeminikerb sewoch degmo yegil tikmachinin kemasaded yalutin chigiroch eske meftiheyachew bedenb discuss madreg. yihinin sil beteley huletuin kidusan abatochin yeminikerb sewoch(betsu'e wekidus Aba Paulosin ena Abune Merkoriyosin malete new).
3. kezih wichi K/Betkristiyanin lematfat yeminrwarwat sewoch degmo k/BETKRISTIYAN yetemeseretechiw BE KIRISTOS dem mehonun banzenega ena arfen quch binil degmo GETA lobona endiseten binteyikew. Keminim neger belay degmo melkam ayeseru yalu ye agelgilot mahiberatin yelele sim eyeseten yeminisadebewn binakom yetim silemanders.
4.be melkam agelgilot lay yalen degmo be agelgilotaachin yebelete binitega.
elalehu
Ye AMLAKACHIN cherinet ye EMEBETACHIN amalaginet ye KIDUSAN miljana tselot KIDIST BETEKRISTIYANIN and yadirgili
Amen
Anonymous said...
ewnet new yalachihut Egziabher yemisanew neger yelemina yihinin tiwlid weyi yilewutew weyim kebetekrstiyan gelel yadrgilin. Abetu ebakih siman,yegnan hatyat satimeleket netsa yehonech agerachin betachin hiywetachin tarikachin selamachin yehonech betekrstiyanachinin nets a awtalin akim yelenim akim hunen Amen
Fikirte A said...
In the name of the holy trinity one divinity amen!

Abetu! yezelalem abat, yeselam aleka medihane-alem kiristos hoy, weden fekiden balametanew zer eyetemekan andituan b/k lemafires yeminitatarewin wede libonachin melisen! lemiyalefew lemitefaw poletica, siltan, lemayazalik sigawi tikim bilen zelalemawituan tewahido kebizu akitacha leminiwegat hulu akimachin min yahil endehone bemitasayibet menged tastemiren timekiren zend enimatsenihalen! Libonachinin bezer-manzer, befikre niway ena be-tihibit tebtibo ye-yazewin telat diabilosin, kefitretat hulu akibirehe bemeretikat beazagnitu enatachin dingil mariam lekso ena milja arikilin!. Yemininafikewin selam, fikir ena andinte be-betihe tatsena zend enileminihalen!!!
Anonymous said...
Dselamoch selewent senger bezuochachen yamenale themawen sel mahbeher kidusan sayehone sele andet betkerstyanachen newena yehnenem le Abe Serake weldeselase be posta lakulachew yehe bedneb esachwen yemlktachwalena eske yekoyen.
Anonymous said...
መልካም፤ አንድ ጥያቄ እንድጠይቅ ይፈቀድልኝ።
አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መሪ ናቸው፤ የጻፉት መጽሐፍ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕምነትና ዶግማ ነውን?
አቶ ክፍሉ ታደሰ የኢሕአፓ አመራር አባል የነበሩ፤ [አሁን ግን እርሳቸው ይወቁት]፤ አንድ መጽሐፍ ስለ ኢሕአፓ ቢጽፉ የኢሕአፓ መርሕ ነበረ ማለት ትንሽነት ነው። የምትተቹበት እውቀቱና ችሎታው ካላችሁ በኦፊሴል ያወጣውን ማኒፌስቶ {ፕሮግራሙን]፤ በየወቅቱ የሚያወጣቸውን አቋሙን ተቹ።
ባልና ሚስት ተጣልተው ሽማግሌ ምክንያታቸውን ሲጠይቃቸው፤ የሚሰጡት ምላሽ እርሱ ለወር ወጪ የሚሰጠን አይበቃኝም፤ እርሷ ስገባ ፊቷን ታጠቁርብኛለች ይሆናል መልሳቸው። ዋናው ምክንያት ግን ሌላ ነው። እናንተም ዋናውን ምክንያታችሁን ለአንባብያን ሸሽጋችሁ በማይሆን ምክንያት ምስኪኑን አንባቢ አታደናግሩ።
ክርስትና ዕውነት ነው ዕውነት መስክሩ። ዕውነቱን የማታውቁት ከሆነ ደግሞ ለመጻፍ አትቸኩሉ።
Anonymous said...
"Anonymous said...

Dear Dejeselam,
You are a living evidence for the inevitable freedom of our beloved church from the tribal thugs, the day time robbers, the taxi driving and parking lot bandits, the ehapa derg & woyane murderers who have been hell bent all along to disrupt, weaken and control the church so that they can spearhead their futile political agenda which usually is designed to oppress the peace loving people and pillage the country Ethiopia. I was hoping that one day Mahiber Kidusan to liberate the church from the stranglehold of the poisonous and parasite Ethiopians, unfortunately it seems that the Mahiber is spineless, dangerous, wicked, and righteous all at once just like the Lucifer. Therefore, the key lies in the hands of independent minded Ethiopians, which i thing the editor/s of this blog sphere rightly represents. Please, use it wisely.
May 21, 2010 6:08 AM "


Dear Editor (Blogger) of DejeSelam,

ከላይ፡በተመለከትው፡አስተያየት፡ላይ፡ያቀረብኩት፡
አስተያየት፡ለምን፡እስካሁን፡እንዳልወጣ፡ለመጠየቅ፡
ነው።ጽሑፌን፡እንዳይወጣ፡የሚያደርግ፡ምን፡ተገኘ
በት?!

መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡
በምሕረቱ፡ይጎብኘን! አሜን።


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።
Anonymous said...
How do we correct the Churches abroad ? Is that taking them to under aba Paulos's administration? you said that it is under woyane's influence. So, what comes first? I think, getting rid of woyane, restore the Church's power and working with the churches should be the order. Aseemingly genuine commentary,but in essence a woyane's approach. What is the solution you think?